የአሰልጣኞች አስተያየት | አርባምንጭ ከተማ 1-1 ሀዲያ ሆሳዕና

የሳምንቱ የመጨረሻ ጨዋታ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጋጣሚ አሰልጣኞች ከሱፐር ስፖርት ጋር ቀጣዩን ቆይታ አድርገዋል።

አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ – አርባምንጭ ከተማ

በውጤቱ ደስተኛ ስለመሆናቸው

ደስተኛ አይደለሁም። በተለይ ደግሞ አስቀድመን ጎል አስቆጥረናል። ያን ማስጠበቅ ብንችል ጥሩ ነበር። ወደ መጨረሻው ላይ እነሱ ጫና ፈጥረዋል። እኛ ደግሞ በመጀመሪያው አጋማሽ የተሻለ ስንቀሳቀስ ነበር። ከአገባን በኋላም የነበረን እንቅስቃሴ ጥሩ ነበር። ጎል ከተቆጠረብን በኋላ ግን ተነሳስተው ነበር።

ስለዕረፍት ጊዜው ጥቅም

ያደረግናቸው ጨዋታዎች ቁጥር አናሳ ነው። አሁም ያደርግናቸው ጨዋታዎች አሉ። ከእነዚህም ተነስተን በጊዜው በመስራት የተሻልን ሆነን እንቀርባለን።

አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት – ሀዲያ ሆሳዕና

ስለሄኖክ አርፌጮ በጊዜ በጉዳት ማውጣት

ሄኖክ የቡድኑ አምበል ነው ፤ በእሱ ቦታ የተጫወተው እያሱም በጣም ጥሩ ነው። ግን አንዳንዴ ተፈጥሯዊ ተጫዋች ቢኖር የተሻለ ይሆናል። እያሱ ግን በሚገባ ቦታውን ተክቶ ስለተጫወተ የተሻለ ነው ብዬ ነው የማስበው። ቢኖር ግን ጥሩ ነበር።

ስለዳኛው የቅጣት ምት ውሳኔ

በእርግጥ ለእኛ ሲታይ ውስጥ ነው። መጨረሻ ላይ ግን በእይታ እሱ ከእኛ ቅርብ ቦታ ላይ ነው ያለው። ለእኛ ሲታይ ግን እንደተጎተተ ይታወቃል። ተጫዋቾችም እንደዛ ሲጮሁ ያለምክንያት አይመስለኝም ፤ ምክንያት ይኖረዋል። ከዚህ በኋላ አይተን ነው የምናረጋግጠው።

ያጋሩ