ዚምባብዌ ከደቡብ አፍሪካ እና ኢትዮጵያ ጋር ላለባት ጨዋታ ለተጫዋቾች ጥሪ አቅርባለች

ኅዳር 5 በሜዳዋ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን የምትገጥመው ዚምባቡዌ ለ26 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርባለች።

በምድብ 7 ተደልድላ ለኳታሩ የዓለም ዋንጫ ለማለፍ ስትጥር የነበረችው ነገርግን ቀድማ መውደቋን ያረጋገጠችው ዚምባቡዌ የምድቡ አምስተኛ እና ስድስተኛ ጨዋታዋን ህዳር 2 እና 5 ከደቡብ አፍሪካ እና ኢትዮጵያ ጋር ታደርጋለች። የቡድኑ አሠልጣኝ ኖርማን ማፔዛም በእነዚህ ጨዋታዎች የሚጠቀሟቸውን 26 ተጫዋቾች ከደቂቃዎች በፊት ይፋ አድርገዋል።

አሠልጣኙም በጉዳት ምክንያት ልምድ ያላቸውን ኖሌጅ ሙሶና እና ቲኔጅ ሀዴቤን በጉዳት ምክንያት ማጣታቸው ታውቋል። በስብስቡም በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ለአስቶን ቪላ የሚጫወተው ማርቭል ናካምባን አይነት ከሀገር ውጪ የሚጫወቱ ተጫዋቾቹ ቢኖሩም አብዛኞቹ ከሀገር ውስጥ ክለቦች እንደተጠሩ ተመላክቷል።