የዋልያዎቹ ቀጣይ ተጋጣሚ ስብስቧን ይፋ አድርጋለች

በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካን የሚገጥሙት ጋናዎች ለወሳኞቹ ጨዋታዎች ለ28 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርበዋል።

ኳታር ለምታስተናግደው የ2022 ዓለም ዋንጫ ለማለፍ የአህጉራችን ብሔራዊ ቡድኖች በምድቦች ተከፋፍለው የማጣሪያ ጨዋታዎችን እያደረጉ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም በምድብ ሰባት ከጋና፣ ደቡብ አፍሪካ እና ዚምባቡዌ ጋር ተደልድሎ የማጣሪያ ፍልሚያውን እየከወነ ቢገኝም ከወዲሁ ሁለት ጨዋታዎች እየቀሩት ከውድድሩ ውጪ ሆኗል። ቡድኑ ከውድድሩ ውጪ ቢሆንም ግን ከጋና እና ከዚምባቡዌ ጋር ለሚደረጉት የምድብ የመጨረሻ የመርሐ-ግብር ማሟያ ጨዋታዎች ለማድረግ ባሳለፍነው ቅዳሜ ምሽት ለ26 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርቦ በትናንትናው ዕለት ዝግጅቱን ጀምሯል። ከደቂቃዎች በፊት የኢትዮጵያ የመጨረሻ ተጋጣሚ ዚምባቡዌ ለ26 ተጫዋቾች ጥሪ ማቅረቧንም ዘግበን ነበር።

ህዳር 2 በደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ከዛ ደግሞ ህዳር 5 የደቡብ አፍሪካ አቻውን የሚገጥመው የጋና ብሔራዊ ቡድንም ከደቂቃዎች በፊት ለ28 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርቧል። ከሁለት ወር በፊት ዳግም የጥቋቁር ከዋክብቶቹ አሠልጣኝ ሆነው የተሾሙት ሰርቢያዊው አሠልጣኝ ሚሎቫን ራጄቫክንም ባሳለፍነው ወር ዚምባቡዌን ከገጠሙበት ስብስብ መጠነኛ ለውጦችን ማድረጋቸውም ታውቋል። በይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫ በተገለፀው የተጫዋቾች ዝርዝር ውስጥ እንደ ቶማስ ፓርቴ፣ ጆርዳን አየው፣ ዳንኤል አማርቲ እና አንድሬ አየው አይነት ስመ ጥር ተጫዋቾችም መኖራቸው ታውቋል።

የተጫዋቾቹ ዝርዝር 👇