ከፍተኛ ሊግ | ለገጣፎ ለገዳዲ በርካታ አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል

የከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ ተወዳዳሪው ለገጣፎ ለገዳዲ አስራ ሰባት አዳዲስ ተጫዋቾች ሲያስፈርም የነባር ተጫዋቾችን ውል አድሷል።

በወጣቱ አሰልጣኝ ጥላሁን ተሾመ እየተመራ የሚገኘውን ቡድን ከተቀላቀሉት ተጫዋቾች መካከል ከዚህ ቀደም ለክለቡ የተጫወተው ልደቱ ለማ ይገኝበታል። በተጠናቀቀው ውድድር ዓመት በመከላከያ ቆይታ የነበረው አጥቂው ወደ ቀድሞ ቤቱ ለሦስተኛ ጊዜ ተመልሷል።

በ2013 ውድድር ዓመት በኮልፌ ቀራኒዮ ቡድን ውስጥ ጥሩ ሲንቀሳቀስ የነበረው ኪሩቤል ወንድሙ ሌላው ፈራሚ ሲሆን አብዱላዚዝ አማን ከኢኮሥኮ፣ አማኑኤል ኤርቦ ከጎፋ ባሪንቺ፣ በፌዴራል ፖሊስ ተስፋ እንቅስቅሴ ያሳየው ብሩክ ብርሀኑ አዲስ ከፈረሙት ተጫዋቾች ናቸው።

ሌሎች ክለቡን የተቀላቀሉት በአማካይ ስፍራ ላይ የሚጫወተው ሰላሙ አለፈ ከአርሲ ነገሌ፣ በወልቂጤ እና አምበሪቾ ሲጫወት የምናውቀው ብስራት ገበየው፣ ተፈራ አንለይ ከኢኮሥኮ፣ ሀብታሙ ዓለማየሁ እና ሱራፌል ኪዳኔ የፈረሙ ተጫዋቹች ናቸው።

የተከለካይ ስፍራ ተጫዋቾቹ መታሰብያ ገዛኸኝ እና ጆቴ ገመቹ ከነገሌ አርሲ፣ ከፌዴራል ፖሊስ አቤል አየለ እና ታምራት አየለ እና ከየካ ፍፁም ጉዱ፣ በግብ ጠባቂ ስፍራ ላይ ከፌዴራል ፖሊስ እስራኤል አለ እና ከመከላካያ ዱሬሳ ነጌሶ ፊርማቸውን ያኖሩ ሌሎች ተጫዋቾች ናቸው።

ክለቡ ከአዲስ ፈራሚዎች ባሻገር የፋሲል አስማማው፣ ዳዊት ቀለመወርቅ፣ አንዋር፣ አብዱልጀባር፣ ታምራት ዘውዴ፣ አስናቀ ተስፋዬ፣ መዝገቡ ቶላ፣ በሽር ደሊል እንዲሁም ዳንኤል ታደሰ ውል ያደሰ ሲሆን ሁለት ወጣት ተጫዋቾችን ከታችኛው ቡድን ማሳደጉን ሶከር ኢትዮጵያ ከክለቡ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡