አምስተኛ ተጫዋች ከብሔራዊ ቡድኑ ስብስብ ውጪ ሆኗል

ከደቡብ አፍሪካው ጨዋታ አስቀድሞ በዝግጅት ላይ የሚገኙት ዋልያዎቹ አንድ ተጨማሪ ተጫዋች ከስብስባቸው ውጪ ሆኗል።

ለ2022 የኳታሩ የዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎችን እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የፊታችን ሐሙስ ከጋና አቻው ጋር ይገናኛል። ከዚህ ጨዋታ አስቀድሞ በንግድ ባንክ ሜዳ ልምምዱን እየሰራ የሚገኘው የአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ስብስብ ዛሬ ተጨማሪ አንድ ተጫዋች ከቡድኑ ውጪ ታውቋል። ከቡድኑ የተለየው ተጫዋች የፋሲል ከነማው የመስመር አጥቂ ሽመክት ጉግሳ ሆኗል። ተጫዋቹ ከስብስቡ ውጪ የሆነበት ምክንያት ደግሞ የግል ጉዳይ መሆኑን ዋና አሰልጣኙ በፌዴሬሽኑ ፅህፈት ቤት እየሰጡ ባለው መግለጫ ላይ ተናግረዋል።

ብሔራዊ ቡድኑ ከዚህ ቀደም ሱራፌል ዳኛቸውን በጡንቻ መሸማቀቅ ፣ ያሬድ ባየህን በብሽሽት ጉዳት ፣ ፋሲል ገብረሚካኤልን በቤተሰብ ሀዘን እንዲሁም እንዲሁም አማኑኤል ገብረሚካኤልን በግል ጉዳይ ምክንያት ማጣቱ ይታወሳል።

– ሽመክት ከቡድኑ ውጪ የሆነው በሀዘን ሳይሆን በግል ጉዳይ በመሆኑ በኤዲት የተስተካከለ መሆኑን እየገለፅን ለተፈጠረው ስህተት ይቅርታ እንጠይቃለን።

ያጋሩ