ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰላለፍ ታውቋል

በዩጋንዳ አስተናጋጅነት ሲካሄድ የቆየው የሴካፋ ከ20 ዓመት በታች ውድድር ዛሬ ፍፃሜውን ሲያገኝ ዩጋንዳን የምትገጥመው ኢትዮጵያ የምትጠቀምበት አሰላለፍን ፌዴሬሽኑ ይፋ አድርጓል።

እኩል 12 ነጥቦች ይዘው በጎል ልዩነት ተበላልጠው ከአናት የተቀመጡት ዩጋንዳ እና ኢትዮጵያ ዛሬ 9:00 ላይ ወሳኙን ጨዋታ የሚያደርጉ ሲሆን ታዳጊዎቹ ሉሲዎች ጨዋታውን ካሸነፉ የውድድሩ ቻምፒዮን ይሆናሉ። በአንፃሩ የተሻለ የጎል ልዩነት ያላት ዩጋንዳ የአቻ ውጤት ለዋንጫ አሸናፊነት በቂዋ ነው።

አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል በዛሬው ጨዋታ የሚጠቀሙበት የመጀመርያ 11 ይህንን ይመስላል:-

ግብ ጠባቂ 

እየሩሳሌም ሎራቶ 

ተከላካዮች

ብዙዓየሁ ታደሰ       
ብርቄ አማረ         
ቤተልሔም በቀለ
ናርዶስ ጌትነት (አ)                                  
አማካዮች

ኝቦኝ የን
ገነት ኃይሉ           
መዓድን ሳህሉ

አጥቂዎች

ረድኤት አስረሳኸኝ       
ቱሪስት ለማ                      
መሳይ ተመስገን

ያጋሩ