ዋልያውን የሚገጥመው የጋና አሰላለፍ ይፋ ሆኗል

ከሰዓታት በኋላ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ወሳኝ ጨዋታ የሚጠብቃቸው ጋናዎች ወደ ሜዳ የሚያስገቧቸው ቀዳሚ ተጫዋቾች ዝርዝር ታውቋል።

ለ2022 ዓለም ዋንጫ ለማለፍ የአህጉራችን ቡድኖች የማጣሪያ ጨዋታቸውን እያደረጉ ሲሆን በምድብ ሰባት የሚገኙት ኢትዮጵያ እና ጋናም የምድብ አምስተኛ ጨዋታቸውን ከሦስት ሰዓታት በኋላ ደቡብ አፍሪካ ላይ ያደርጋሉ። ድረ-ገፃችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን አስተላለፍ ቀድማ ያወጣች ሲሆን አሁን ደግሞ የተጋጣሚዋን አሰላለፍ የጋና ብዙሃን መገናኛዎች ይፋ አድርገዋል። አሠልጣኝ ሚሎቫን ራጄቫክን ከስር የተዘረዘሩትን ተጫዋቾች ወደ ሜዳ የሚያስገቡ ይሆናል።

16 ጆጆ ዎላኮት
2 አንድሪው ይያዶም
17 ባባ ራህማን
15 ጆሴፍ አይዶ
18 ዳንኤል አማርቴ
21 ኢድሪሳ ባባ
20 መሐመድ ቁዱስ
9 ጆርዳን አዬው
10 አንድሬ አዬው
14 ቦክዬ ያዶም
22 ከማል ዲን

ያጋሩ