የከፍተኛ ሊጉ ክለብ አርሲ ነገሌ በርካታ አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የነባሮችንም ውል ለተጨማሪ ዓመት አራዝሟል፡፡
በቅርቡ የቀድሞው አሰልጣኙ ራህመቶ መሐመድን በድጋሚ አሰልጣኙ አድርጎ የቀጠረው የከፍተኛ ሊጉ የምድብ ሐ ተካፋዩ አርሲ ነገሌ ለ2014 የውድድር ዘመን ብርቱ ተፎካካሪ ሆኖ ለመገኘት የአዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር የፈፀመ ሲሆን በክለቡ የነበሩ ነባር ተጫዋቾችን ውል በማራዘም የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን ጀምሯል፡፡
ክለቡ የምክትል አሰልጣኙ በሽር አብደላን ውል ያደሰ ሲሆን አስራ ስድስት አዳዲስ ተጫዋቾችንም የግሉ አድርጓል። ሰዒድ ሮባ (ግብ ጠባቂ ከሞጆ ከተማ) ፣ አባቱ ኢጃሮ (ግብ ጠባቂ ከቡሌ ሆራ) ፣ ምንተስኖት አሸናፊ (ግብ ጠባቂ ከደቡብ ፖሊስ) ፣ አሊ ቡና (ተከላካይ ከቡሌ ሆራ) ፣ መሳፍንት ነጋሽ (ተከላካይ ከሞጆ ከተማ) ፣ ዮናስ ፍቃዱ (ተከላካይ ከሞጆ ከተማ) ፣ ታዬ ጋሻው (ተከላካይ ከአዳማ ተስፋ) ፣ ወንድወሰን ሊሬ (ተከላካይ ከአዲስ አበባ ከተማ) ፣ ዝነኛው ጋዲሳ (አማካይ ከሱሉልታ) ፣ ብሩክ ብፁህአምላክ (ከቢሾፍቱ ከተማ) ፣ አቡበከር ኑሪ (ተከላካይ ከባቱ ከተማ) ፣ አቤል ማሙሽ (አጥቂ ከሞጆ) ፣ ሰይፉ ታከለ (ከሀረር ሲቲ አጥቂ) ፣ ኦኒ ኡጁሉ (አጥቂ ከቤንች ማጂ ቡና) ፣ ምስጋና ግርማ (አጥቂ ከሞጆ) እና ኤፍሬም ቶማስ (አጥቂ ከመድን) አዲሶቹ ፈራሚዎች ናቸው፡፡
ክለቡ ነባር የሆኑትን ጫላ ተስፋዬ ፣ ኢሳ አህመድ ፣ ቱፋ ተሽቴ ፣ ፍቅሩ ጴጥሮስ ፣ ምትኩ ጌታቸው ፣ አቤል ፋንታ የተባሉትን ውል ሲያድስ ዱሬሳ ገመቹ ፣ ሰለሞን ገመቹ እና ጀማል ፈይሶ የተባሉ ወጣቶችን መልምሎ በቢጫ ተሴራ ስለመያዙ ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ ባደረሰው መረጃ አካቶ ጠቁሟል፡፡