አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች | አርባምንጭ ከተማ ከ ባህር ዳር ከተማ

ለብሄራዊ ቡድን ጨዋታዎች የ20 ቀናት እረፍት የወሰደው የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አርባምንጭ ከተማ እና ባህር ዳር ከተማ በሚያደርጉት ጨዋታ ይመለሳል። የአራተኛ ሳምንት የመክፈቻ ጨዋታን የተመለከቱ ወቅታዊ መረጃዎችንም እንደሚከተለው አሰናድተናል።

በወረቀት ላይ ባለሜዳ የሆኑት አርባምንጭ ከተማዎች ከሦስት ሳምንታት በፊት ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር ነጥብ ከተጋሩበት የመጀመሪያ አሰላለፍ አንድ ለውጥ ብቻ አድርገው ወደ ሜዳ ለመግባት ተዘጋጅተዋል። በዚህም ጉዳት ላይ የሚገኘው አንድነት አዳነ ብቻ በአሸናፊ ፊዳ ተለውጧል።

እንደ ተጋጣሚያቸው አርባምንጭ ሁሉ በሦስተኛ ሳምንት አንድ ነጥብ ያገኙት ባህር ዳር ከተማዎች ደግሞ ከመጨረሻው ፍልሚያቸው የግብ ዘቡ ፋሲል ገብረሚካኤልን በአቡበከር ኑሪ፣ አህመድ ረሺድን በመሳይ አገኘው፣ ፎዐድ ፈረጃን በሳላምላክ ተገኘ እንዲሁም መናፍ ዐወልን በዜናው ፈረደ ተክተው ጨዋታውን ቀርበዋል።

ከቀድሞው አሰልጣኛቸው አብርሀም መብራቱ ጋር መገናኘታቸውን አስመልክቶ ለአሰለጠኗቸው አሰልጣኞች ክብር እንዳላቸው የገለፁት አሰልጣኝ መሳይ ከዚህ ቀደሙ ቡድናቸው ፍጥነት ጨምሮ እንደሚጫወት ጠቁመዋል። አሰልጣኝ አብርሀም በበኩላቸው ዕረፍቱ ቡድናቸውን ለማዘጋጀት እንደጠቀማቸው አንስተው የቀደመ ተጫዋቾቻቸውን በአሰልጣኝነት ሲገጥሙ ትልቅ ደስታ እንደሚፈጥርባቸው ተናግረዋል።

የሁለቱን ቡድኖች ጨዋታ ኢንተርናሽናል ዳኛ በላይ ታደሠ በአልቢትርነት የሚመሩት ይሆናል።

የሁለቱ ቡድኖች አሰላለፍ የሚከተለው ነው።

አርባምንጭ ከተማ

1 ሳምሶን አሰፋ
14 ወርቅይታደሰ አበበ
15 በርናርድ ኦቼንግ
4 አሸናፊ ፊዳ
2 ተካልኝ ደጀኔ
23 ሀቢብ ከማል
20 እንዳልካቸው መስፍን
21 አንዱአለም አስናቀ
22 ፀጋዬ አበራ
26 ኤሪክ ካፒያቶ
9 በላይ ገዛኸኝ

ባህር ዳር ከተማ

91 አቡበከር ኑረሪ
16 መሳይ አገኘው
15 ሰለሞን ወዴሳ
2 ፈቱዲን ጀማል
7 ግርማ ዲሳሳ
27 አብዱልከሪን ንኪማ
25 አለልኝ አዘነ
14 ፍፁም ዓለሙ
18 ሳላምላክ ተገኘ
11 ዜናው ፈረደ
77 ኦሴ ማዉሊ

ያጋሩ