አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች | ወልቂጤ ከተማ ከ ሀዋሳ ከተማ

የአራተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ሁለተኛ ጨዋታን የተመለከቱ አሁናዊ መረጃዎች እንድትካፈሉ እንደሚከተለው አዘጋጅተናቸዋል።

ሊጉ ለብሔራዊ ቡድን እረፍት ከመቋረጡ በፊት ከባህር ዳር ከተማ ጋር ነጥብ የተጋሩት ወልቂጤ ከተማዎች የዓመቱ የመጀመሪያ ድላቸውን ማግኘትን በማሰብ ከመጨረሻው ጨዋታቸው ሦስት ለውጦችን አድርገው ወደ ሜዳ ገብተዋል። በዚህም ሀብታሙ ሸዋለም፣ ጫላ ተሺታ እና አህመድ ሁሴን በእስራኤል እሸቱ፣ ሙሉጌታ ወልደጊዮርጊስ እና ያሬድ ታደሰ ተተክተዋል።

በተቃራኒው ከሲዳማ ቡና ጋር ያደረጉትን ከባዱን ጨዋታ ረተው ሊጉ የተቋረጠባቸው ሀዋሳ ከተማዎች ደግሞ በቃሉ ገነነን ብቻ በሄኖክ ድልቢ ለውጠው ጨዋታውን ቀርበዋል።

12 ሰዓት ሲል የሚጀምረው ጨዋታን ጨዋታ ፌዴራል ዳኛ ተካልኝ ለማ በአልቢትርነት የሚመሩት ይሆናል።

ቡድኖቹ ወደ ሜዳ ይዘዋቸው የሚገቡት ተጫዋቾች ዝርዝርም የሚከተለው ነው።

ወልቂጤ ከተማ

1 ሲልቪያን ግቦሆ
12 ተስፋዬ ነጋሽ
19 ዳግም ንጉሴ
24 ውሀብ አዳምስ
3 ረመዳን የሱፍ
8 በኃይሉ ተሻገር
13 ሙሉቀን ወልደጊዮርጊስ
14 አብዱልከሪም ወርቁ
11 እስራኤል እሸቱ
20 ያሬድ ታደሰ
9 ጌታነህ ከበደ

ሀዋሳ ከተማ

77 መሐመድ ሙንታሪ
7 ዳንኤል ደርቤ
26 ላውረንስ ላርቴ
5 ፀጋሰው ድማሙ
13 አቡዱልባሲጥ ከማል
19 ዮሐንስ ሴጌቦ
25 ሄኖክ ድልቢ
29 ወንድማገኝ ኃይሉ
21 ኤፍሬም አሻሞ
17 ብሩክ በየነ
10 መስፍን ታፈሰ

ያጋሩ