የ2013 የውድድር ዘመን የኮከቦች ምርጫ ላይካሄድ ይችል ይሆን ?

በአምስት የውድድር ዘርፍ መካሄድ የሚገባው የ2013 የውድድር ዘመን የኮኮበች ሽልማት እስካሁን አለመካሄዱ ለምን ይሆን ?

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከዚህ ቀደም ውድድሮቹ በሚጠናቀቁበት ሜዳዎች ያደርግ የነበረውን የኮኮቦች ምርጫን በማስቀረት ከ2009 ጀምሮ ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ በአንድ በተመረጠ ሆቴል ሽልማት ሥነ ስርዓቱን እያካሄደ መቆየቱ ይታወሳል።

የ2013 የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በስሩ የሚያካሂዳቸው የሴቶች አንደኛ እና ሁለተኛ ዲቪዚዮን የከፍተኛ እና የአንደኛ ሊግ እንዲሁም ከ20 ዓመት በታች ውድድሮች ኮከብ ተጫዋቾች፣ ግብ አስቆጣሪዎች፣ አሰልጣኞች፣ ምስጉን ዳኞች እና ልዩ ተሸላሚዎች ሽልማት እስካሁን አልተካሄደም። ውድድሮቹ ከተጠናቀቁ ከስድስት ወራት በላይ ቢያስቆጥሩም እስካሁን የኮኮብ ምርጫውን ፌዴሬሽኑ በጊዜው አለመካሄዱ ለምን ይሆን ብለን በፌዴሬሽኑ በኩል ለማጣራት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው የተሳካ ባይሆንም እየወጡ እንዳሉ መረጃዎች ከሆነ የ2013 የውድድር ዘመን የኮከቦች ምርጫ በተለያዩ ምክንያቶች ስለመቅረቱ እየተነገረ ይገኛል።

በዚህ ዙርያ የሚኖሩ አዳዲስ ነገሮች ካሉ ተከታትለን የምንመለስበት ይሆናል።

ያጋሩ