የዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ የሆነው የሀዲያ ሆሳዕና እና አዳማ ከተማ ጨዋታን የተመለከቱ ወቅታዊ መረጃዎች እንደሚከተለው አሰናስለናቸዋል።
በሦስተኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታ ከአርባምንጭ ከተማ ጋር ነጥብ የተጋሩት ሀዲያ ሆሳናዎች የዓመቱ የመጀመሪያ ድላቸውን ለማግኘት ከመጨረሻው ጨዋታ ሄኖክ አርፊጮን በቃለአብ ውብሸት፣ ኤሊያስ አታሮን በመላኩ ወልዴ፣ ፍቅረእየሱስ ተወልደብርሃንን በአበባየሁ ዮሐንስ እንዲሁም ሀብታሙ ታደሰን በኢያሱ ታምሩ ለውጠዋል።
በተቃራኒው በወላይታ ድቻ ተሸንፎ የነበረው አዳማ ከተማ ደግሞ ወደ ድል ለመመለስ ሦስት ለውጦችን አድርጎ ጨዋታውን ቀርቧል። በዚህም የቡድኑ አሠልጣኝ ፋሲል ተካልኝ በግብ ብረቶቹ መካከል የሚቆመውን ሴኩምባ ካማራን በጀማል ጣሰው ተከላካዩ አሚኑ ነስሩን በጀሚል ያቆብ እንዲሁም አጥቂው አቡበከር ወንድሙን በአብዲሳ ጀማል ለውጠዋል።
“የየእረፍቱን ጥቅም እና ጉዳት ዛሬ ነው የምናውቀው። ለኛ ጠቅሞናል ብዬ አስባለው። ጨዋታውም ግዴታ ያስፈልገናል። እጅግ በጣም ስለምንፈልገውም በቂ ዝግጅት አድርገናል” አድርገናል ብለው የሀዲያው አሠልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት ሲናገሩ የአዳማው አሠልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ደግሞ “እንደዚህ አይነት የውድድር መቆራረጥ መኖሩ አስቸጋሪ ነው። አሰልቺም ነው የሚሆነው። በነበሩት ቀናትም ክፍተቶቻችን ላይ ሰርተናል። እያንዳንዱ ጨዋታ ለኛ አስፈላጊ ነው።” የሚል ሀሳባቸውን ከጨዋታው ጅማሮ በፊት ሰጥተዋል።
ይህንን ጨዋታ ፌዴራል ዋና ዳኛ ምስጋናው መላኩ የሚመሩት ሲሆን ቡድኖቹም ወደ ሜዳ ይዘዋቸው የሚገቡት የመጀመሪያ አሰላለፍ የሚከተለው ነው።
ሀዲያ ሆሳዕና
1 ሶሆሆ ሜንሳህ
5 ቃለአብ ውብሸት
12 ብርሀኑ በቀለ
16 ፍሬዘር ካሳ
19 መላኩ ወልዴ
14 ኢያሱ ታምሩ
21 ተስፋዬ አለባቸው
27 አበባየሁ ዮሐንስ
8 ሳምሶን ጥላሀን
31 ዑመድ ዑኩሪ
9 ባዬ ገዛኸኝ
አዳማ ከተማ
30 ጀማል ጣሰው
5 ጀሚል ያዕቆብ
4 ሚሊዮን ሰለሞን
80 ቶማስ ስምረቱ
8 አማኑኤል ጎበና
22 ዮናስ ገረመው
6 ዮሴፍ ዮሃንስ
7 ደስታ ዮሀንስ
12 ዳዋ ሆቴሳ
10 አብዲሳ ጀማል
9 አሜ መሀመድ