ከደቂቃዎች በኋላ የሚጀምረውን የአራተኛ ሳምንት የሦስተኛ ቀን ሁለተኛ ጨዋታን የተመለከቱ ወቅታዊ መረጃዎች አሰባስበን ቀርበናል።
እስካሁን ከገጠሟቸው ሦስት ክለቦች ሦስት ነጥብ ማግኘት ያልቻሉት ጅማ አባጅፋሮች በሊጉ መሪ ፋሲል ከነማ አራት ለምንም ከተረቱበት ጨዋታ አራት ለውጦችን አድርገዋል። በዚህም ግብ ጠባቂው ዮሐንስ በዛብህን በአላዛር ማርቆስ፣ ተስፋዬ መላኩን በሙሴ ከበላ፣ አስናቀ ሞገስን በብሩክ አለማየሁ እንዲሁም ሽመልስ ተገኝን በትንሳኤ ያብጌታ ለውጠዋል።
በሰከንዶች ልዩነት በተቆጠሩ ሁለት ግቦች ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር አቻ የተለያዩት ድሬዳዋ ከተማዎች ደግሞ አንድም የተጫዋች ለውጥ ሳያደርጉ ወደ ሜዳ ገብተዋል።
ከጨዋታው መጀመር በፊት የጅማ አባጅፋሩ አሠልጣኝ አሸናፊ በቀለ “እረፍቱ ጠቅሞናል ብዬ አስባለሁ። አንድ ስድስት ተጫዋቾች ከተለያዩ የወጣት ቡድኖች ቀላቅለናል። በዛሬው ጨዋታ አራቱ ቋሚ ተሰላፊዎች ናቸው። የዛሬው ጨዋታ ለእኔ ቀላል ነው።” የሚል ሀሳብ ሲሰጡ የድሬዳዋው አሠልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ደግሞ “በእረፍቱ ከባለፈው ሦስት ጨዋታዎች ክፍተቶች ተነስተን ስንሰራ ነበር። ለዛሬውም ጨዋታ በዚህ መልክ ተዘጋጅተናል። በተቻለ መጠን አጥቅተን ተጫውተን ለማሸነፍ እንገባለን።” በማለት ለሱፐር ስፖርት ተናግረዋል።
ፌዴራል ዳኛ በፀጋው ሽብሩ ይህንን ጨዋታ በአልቢትርነት እንዲመሩት ተመድበዋል።
ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያ አሰላለፍ የሚጠቀሟቸው ተጫዋቾች ደግሞ የሚከተሉት ናቸው።
ጅማ አባጅፋር
30 አላዛር ማርቆስ
20 በላይ አባይነህ
18 ያብስራ ሙሉጌታ
ትንሳኤ ያብጌታ
9 ዱላ ሙላቱ
12 ሮጀር ማላ
9 ሙሴ ከበላ
22 ብሩክ አለማየሁ
24 መሐመድ ኑርናስር
3 መስዑድ መሐመድ
17 ዳዊት ፍቃዱ
ድሬዳዋ ከተማ
30 ፍሬው ጌታሁን
2 እንየው ካሳሁን
13 መሳይ ጳውሎስ
20 መሐመድ አብዱለጢፍ
4 ሄኖክ ኢሳይያስ
16 ብሩክ ቃልቦሬ
5 ዳንኤል ደምሴ
19 ሙኸዲን ሙሳ
15 አውዱ ናፊዩ
9 ጋዲሳ መብራቴ
25 ማማዱ ሲዲቤ