ድሬዳዋ ከተማ ከረጅም ጊዜ በኃላ ሦስት ጎል አስቆጥሮ ጅማ አባ ጅፋርን ከረታበት ጨዋታ በኃላ አሰልጣኞቹ ለሱፐር ስፖርት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ – ድሬዳዋ ከተማ
ሁለቱ አጋማሽ ምን መልክ ነበራቸው
የመጀመርያው አጋማሽ ጥሩ ነበር። ሁለተኛው አጋማሽ ግን በዛ መልክ አልሄደም። ግን እንደ አጠቃላይ ልጆቼ አድርጉ ያልኳቸውን ነገሮች ነው ያደረጉት። በተለይ ሲዲቤ የጨዋታው ልዩነት ፈጣሪ ነበር። ስለዚህ ተጫዋቾቼ ከጨዋታ ጨዋታ መሻሻል እና እድገት እንዳለ፤ ይህ ቡድን ረጅም ርቀት መሄድ እንደሚችል ያየንበት ነው።
ሁለተኛው አጋማሽ ውጤት ለማስጠበቅ አስበው ይሆን
እንዲህ ዓይነት ስሜት አልነበረንም። እንደ ቡድን ተጫውተን እንደዚህ አይነቶችን አጋጣሚ አግኝተህ የጎል ልዮነቶች ስለነበሩብን ጎል ማስቆጠር ደረጃው ላይ ልዩነት ስለሚፈጥር ጎል ለማስቆጠር ፈልገን ነበር። ግን ከእረፍት በኃላ እንቅስቃሴው ወረድ ያለ ነበር። በቀጣይ ጨዋታ ላይ እርሱ ላይ ሰርተን የምንመጣ ይሆናል።
በጅማ በኩል ወጣቶችን ስለ መግጠማቸው
እንዲህ ያለ ነገር አልነበረም። እንደዛ ከሆነ ሦስት በቢጫ ቲሴራ የተሻሉ ወጣቶች እኛ ተጠቅመናል። እኔጨዋታውን በዚህ መልክ አላየውም። ሦስት ነጥብ ስለማሸነፍ ነው አስበን የገባነው። እንደ አጠቃላይ ቡድኔ ባሳየው አቋም ደስተኛ ነኝ።
ስለ ማማዱ ሲዲቤ የቡድኑ ቁልፍ አጥቂነት
እንደዚህ እገምታለው። ከአራት ቀን በኃላ ከወልቂጤ ጋር ጨዋታ አለን እንዲያርፍ እፈልጋለው ግን ሜዳ ላይ ያቆየሁት ከጎል ጋር ያለው ነገር ጥሩ ስለሆነ በውድድሩም በጎል አስቆጣሪነት ረጅም ርቀት ይሄዳል ብዬ አስባለው። እንዳ አጠቃለይ ማማዱ ሲዲቤ የጨዋታው ልዩነት ፈጣሪ ነበር።
የነጥባቸው ከፍ ማለት እና ቀጣይ አላማ
በርግጥ ገና አራተኛ ጨዋታ ነው። ነገር ግን በተቻለ መጠን ከመሪዎቹ ጋር እግር እግር እየሄድን ከስር ከስር መከተል እንፈልጋለን። ከዛ አንፃር አሁን ያለንበት ነገር ጥሩ ነው ብዬ አስባለው።
አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ- ጅማ አባ ጅፋር
ስለተመዘገበው ውጤት
የመጀመርያው ደቂቃዎች የተቆጠሩብን ጎሎች ዋጋ አስከፍለውናል። እንደዚህ ያለ ውጤት ይመጣል ብዬ አልጠበኩም። መዘናጋቶች አሉ ተጫዋቾቹ ገና ጀማሪ ስለሆኑ ክፍተቶች ያሳያሉ በተለይ ግብጠባቂ አካባቢ እዚህ ላይ እያስተካከልን እሄዳለው ብዬ አስባለው።
በሁለተኛው አጋማሽ ስለመሻሻላቸው
የታክቲክ ለውጥም አለ ተጫዋቾች ኳስን በሚያገኙበት እና በሚያጡበት ጊዜ እንዲተገብሩት የሰራናቸው ስራዎች ነበሩ። እነዛ ነገሮች ጥሩ ነገር ፈጥረውልናል። አሁንም አጨራረስ ላይ ማስተካከል ያለብን ነገር አለ
ወጣቶችን በመጠቀም ስለወሰዱት ኃላፊነት
ትክክለኛ ውሳኔ ነው የወሰንኩት፤ አሁንም ጎሉን ያገባው ልጅ እንዳያችሁት ከታች የመጣ ታዳጊ ነው። ሌሎቹም ወጣቶች ያላቸውን አቅም አሳይተዋል። ስለዚህ በዚህ መልኩ የተሻለ ቡድን በቀጣይ ይዘን እንቀርባለን።
እስካሁን ሦስት ነጥብ ያለማግኘታቸው ጫና
ጫና ውስጥ እገኛለው ብዬ አላስብም። የማሰወተካክላቸው ነገሮች ናቸው። ውድድሩ ሰፊ ነው። በርግጥ በተከታታይ አራት ጨዋታ ሽንፈት ማስተናገድ ከባድ ነው። አርመን የተሻልን ሆነን እንመጣለን።