ከተጫዋቾች ዝውውር ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም በአራት ተጫዋቾች የፍርድ ቤት ዕግድ የተላለፈበት ሀድያ ሆሳዕና አሁን በአንድ ተጫዋች ክስ ምክንያት እግድ መተላለፉ ታውቋል።
የ2013 የውድድር ዘመን ለሀዲያ ሆሳዕና ሲጫወት የቆየው አዲስ ህንፃ ከክለቡ ጋር በተስማማሁት መሠረት በቼክ የተቀበልኩት አምስት መቶ ሰባ ስድስት ሺህ ብር አልተከፈለኝም በማለት በአቶ ብርሐኑ በጋሻው የሕግ አማካሪ ጠበቃ እና የአግር ኳስ ስፖርትኞች ሕጋዊ ወኪል አማካኝነት ጉዳዩን ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት በማምራት ሲከታተል ቆይቷል።
በመጨረሻም ልደታ 5ኛ ምድብ የፍ/ብሔር ችሎት በሀድያ ሆሳዕና ላይ ከሊግ ካምፓኒው ከሚያገኘው ድርሻ አምስት መቶ ሰባ ስድስት ሺህ ብር አግዶ እንዲቆይ ውሳኔ አሳልፏል።
ይህን እግድ ተከትሎ ሀዲያ ሆሳዕና ከሊግ ካምፓኒው ከሚያገኘው የገቢ ክፍፍል ላይ በአጠቃላይ 2.57 ሚልዮን ብር ታግዶበት የሚቆይ ይሆናል።