ኢትዮጵያዊያን ዳኞች የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫን ይመራሉ

አራት ኢትዮጵያዊያን ዳኞች የኮንፌዴሬሽን ጨዋታን ለመምራት አመሻሽ ወደ ወደ ዲሞክራቲክ ኮንጎዋ ዋና ከተማ ኪንሻሳ ያቀናሉ፡፡

የካፍ የ2021 የኮንፌዴሬሽን ጨዋታዎች በያዝነው ሳምንት መደረጋቸውን ሲቀጥሉ ከቻምፒዮንስ ሊጉ የማጣሪያ ጨዋታዎች ውጪ የነበሩት የዲሞክራቲክ ኮንጎው ኤ ኤስ ማኒዬማ ዩኒየን ከግብፁ ፒራሚድ ክለብ ጋር የኮንፌዴሬሽን የፕሌይ ኦፍ መርሀ-ግብራቸውን ኪንሻሳ በሚገኘው ስታድ ዴ ማርቲርስ በተባለው አርቴፊሻል ሜዳ ላይ የፊታችን ዕሁድ ምሽት 12፡00 ላይ ይጫወታሉ፡፡

ይህንን ጨዋታ አራት ኢትዮጵያዊያን የሚመሩት ሲሆን ወደ ስፍራውም ዛሬ ምሽት ያመራሉ፡፡ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ እየዳኙ የሚገኙት በላይ ታደሰ በመሐል ዳኝነት፣ ክንዴ ሙሴ እና ትግል ግዛው በረዳት ዳኝነት የተመደቡ ሲሆን አራተኛ ዳኛ በመሆን ደግሞ ለሚ ንጉሤ ወደ ስፍራው እንደሚያቀኑ ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች፡፡ ሩዋንዳዊው አሌክሲስ ረዳምፕተስ ደግሞ የጨዋታ ታዛቢ ናቸው፡፡