በሦስት ምድብ ተከፍሎ ታህሳስ ወር መጀመርያ ላይ እንደሚጀመር የሚጠበቀው የከፍተኛ ሊግ ክለቦች የምድብ ድልድል ተለይቶ ታውቋል።
የ2014 የውድድር ዘመን የከፍተኛ ሊግ ክለቦች የዕጣ ማውጣት ሥነ ስርዓት እና የደንብ ውይይት የፌዴሬሽኑ አካላት ተሳታፊ ክለቦች በተገኙበት በጁፒተር ሆቴል ተካሂዷል። ክፍያ የፈፀሙ 23 ክለቦች ብቻ የዘንድሮ ውድድር እንዲካፈሉ ሲደረግ ጋሞ ጨንቻ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ከንባታ ሺንሺቾ፣ አርሲ ነገሌ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ፣ ጅማ አባቡና ክፍያ ባለመፈፀማቸው ከውድድሩ ውጪ ተደርገዋል። እስከ አርብ ባለው ቀነ ገደብ ክፍያ ከፈፀሙ በድልድል ውስጥ ይካተታሉም ተብሏል።
አሁን ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ወልድያ፣ እንጅባራ ከተማ፣ ዳሞት ከተማ፣ ወሎ ኮምቦልቻ፣ ደሴ ከተማ እና ሰሜን ሸዋ ደብረ ብርሀን እንደማይሳተፉ ሲታወቅ ሁኔታዎች ወደነበሩበት ሲመለሱ ሊካተቱ እንደሚችሉ ተገልጿል።
በምድብ አደላደሉ ዙርያ አከራካሪ ውይይቶች ከተካሄዱ በኃላ በስተመጨረሻም ተከታዩ ድልድል በዕጣ ሊወጣ ችሏል። በዚህ መሠረት:-
ምድብ ሀ
ገላን ከተማ
አምቦ ከተማ
ኢትዮ ኤሌክትሪክ
ሻሸመኔ ከተማ
ሀላባ ከተማ
ጌዲዮ ዲላ
ባቱ ከተማ
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
በምድብ ለ
ስልጤ ወራቤ
ለገጣፎ ለገዳዲ
ቡታጅራ ከተማ
ከፋ ቡና
ቤንች ማጂ ቡና
ቡራዩ ከተማ
ቂርቆስ ክ/ከተማ
ሰንዳፋ በኬ ከተማ
በምድብ ሐ
ሀምበርቾ ዱራሜ
ፌደራል ፖሊስ
ኢትዮጵያ መድን
ነቀምት ከተማ
ጉለሌ ክ/ከተማ
የካ ክፍለ ከተማ
ደቡብ ፖሊስ
ይህን ተከትሎ የምድብ ሀ ጨዋታዎች ሆሳዕና ከተማ፣ የምድብ ለ ጨዋታዎች ሀዋሳ ከተማ እንዲሁም የምድብ ሐ ጅማ ከተማ እንደሚካሄድ ታውቋል።