አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች | መከላከያ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

በአራተኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታን አሁናዊ መረጃዎች አሰባስበን ቀርበናል።

ከተከታታይ ሁለት ድል በኋላ በአዲስ አበባ ከተማ ሦስት ለምንም ተረተው ለዛሬው ጨዋታ የቀረቡት መከላከያዎች በቅጣት ምክንያት ከጨዋታው ውጪ የሆነው ገናናው ረጋሳን ጨምሮ ሰመረ ሀፍታይን እና ልደቱ ጌታቸውን በአለምአንተ ካሳ፣ ቢኒያም በላይ እና ብሩክ ሰሙ ለውጠዋል።

በሦስተኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ነጥብ ተጋርተው የነበረው ቅዱስ ጊዮርጊሶች ደግሞ በቤተሰብ ሀዘን ምክንያት ከስብስቡ ውጪ የሆነው ቸርነት ጉግሳን በሱሌይማን ሀሚድ፣ እስማኤል ኦሮ-አጎሮን በአማኑኤል ገብረሚካኤል እንዲሁም ደስታ ደሙን በከነዓን ማርክነህ ተክተዋል።

“ወደ 19 አዳዲስ ተጫዋቾች በክረምቱ የዝውውር ጊዜ አምጥተን ስለነበር እነሱን ለማቀናጀት እረፍቱ ጊዜ ሰጥቶናል። ብቻ ሀምሳ ሀምሳ ነው ከእንደዚህ አይነት ቡድን (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ጋር ስትጫወት መዘጋጀት በደንብ አለብህ።” የሚል ሀሳባቸውን የመከላከያው አሠልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ሲሰጡ የቅዱስ ጊዮርጊሱ ምክትል አሠልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ ደግሞ “የነበረው የእረፍት ጊዜ በጣም ጠቅሞናል። የዛሬው ጨዋታ ጠንካራ ነው የሚሆነው።” በማለት የቅድመ ጨዋታ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።

ይህንን ተጠባቂ ጨዋታ ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ቴዎድሮስ ምትኩ በአልቢትርበት የሚመሩት ይሆናል።

ቡድኖቹ ተከታዮቹን ተጫዋቾች በመጀመሪያ አሰላለፍ አካተው ወደ ሜዳ የሚገቡ ይሆናል።

መከላከያ

30 ክሌመንት ቦዬ
11 ዳዊት ማሞ
2 ኢብራሂም ሁሴን
4 አሌክስ ተሰማ
24 ቢኒያም በላይ
25 ኢማኑኤል ላርዬ
6 አለምአንተ ካሳ
5 ግሩም ሀጎስ
7 ብሩክ ሰሙ
10 አዲሱ አቱላ
18 ኡኩቱ ኢማኑኤል

ቅዱስ ጊዮርጊስ

30 ኩዋንጎ ቻርለሰ
14 ሄኖክ አዱኛ
24 ፍሪምፖንግ ሜንሱ
4 ምኞት ደበበ
2 ሱለይማን ሀሚድ
5 ሀይደር ሸረፋ
18 ከነአን ማርክነህ
20 በረከት ወልዴ
10 አቤል ያለው
11 አማኑኤል ገብረሚካኤል
7 ቡልቻ ሹራ

ያጋሩ