
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የመወዳደሪያ ስታዲየሞች ታውቀዋል
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የ2014 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ እና ከፍተኛ ሊግ ውድድሮችን የእጣ ማውጣት መርሐ-ግብር በአሁኑ ሰዓት ከተሳታፊ ክለቦች ጋር በመሆን እያወጣ ይገኛል። እጣ ከመውጣቱ በፊትም የሁለቱ ውድድሮች የመወዳደሪያ ስታዲየሞች ይፋ ሆነዋል።
በዚህም የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ በሀዋሳ ከተማ የሚደረግ ሲሆን የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ ውድድር ደግሞ በባቱ ከተማ እንደሚከናወን ተገልጿል።
ስታዲየሞቹ ይፋ ሲሆኑም ኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የውድድር ዳይሬክተር አቶ ከበደ ውድድሮቹን በአንፃራዊነት ሰላማዊ በሆኑ ቦታዎች ላይ ለማድረግ እንደታሰበ አብራርተዋል። ከዚህ ውጪ በሀገራችን ያለው የስታዲየሞች ጥራትም ታሳቢ እንደተደረገ አውስተዋል።
ተዛማጅ ፅሁፎች
“በጀመርነው ፎርማት ውድድራችንን እንቀጥላለን” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2014 ኮከቦቹን በሸራተን አዲስ ሆቴል ዛሬ አመሻሹን ይሸልማል፡፡ ከሽልማት ስነ ሥርዓቱ አስቀድሞ የፕሪምየር ሊጉ አክሲዮን ማኅበር...
ጦሩ ከአጥቂው ጋር ተለያይቷል
ከወራት በፊት መከላከያን የተቀላቀለው ጊኒያዊው አጥቂ ውሉን በስምምነት ቀዶ ዛሬ ወደ ሀገሩ አምርቷል። የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ነገ ከመከፈቱ በፊት በርካታ...
አቡበከር ናስር የጎፈሬ ብራንድ አምባሳደር ሆኖ ነገ ይፈራረማል
ሀገር በቀሉ የትጥቅ አምራች ተቋም ጎፈሬ የወቅቱን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ኮከብ አቡበከር ናስር የብራንድ አምባሳደሩ ለማድረግ ነገ ስምምነት ይፈፅማል። የሀገር...
ኢትዮጵያ ቡና ከተጨማሪ ሦስት ተጫዋቾቹ ጋር በስምምነት ተለያይቷል
ከደቂቃዎች በፊት ከታፈሰ ሰለሞን ጋር መለያየቱን የዘገብነው ኢትዮጵያ ቡና ከተጨማሪ ሦስት ተጫዋቾች ጋር በተመሳሳይ ለመለያየት ከስምምነት ላይ መድረሱ ታውቋል። ኢትዮጵያ...
ኢትዮጵያ ቡና ከአማካይ ተጫዋቹ ጋር ለመለያየት ተስማምቷል
የዝውውር መስኮቱ ሊከፈት ሰዓታት በሚቀሩበት ወቅት ኢትዮጵያ ቡና ከአንድ ተጫዋቹ ጋር ለመለያየት ተስማምቷል። ኢትዮጵያ ቡና በቀጣይ ዓመት ራሱን አጠናክሮ ለመቅረብ...
አሠልጣኝ ካሣዬ አራጌ ውላቸው ከዛሬ ጀምሮ ይቋረጣል
አሠልጣኝ ካሣዬ አራጌ ቀሪ የአንድ ዓመት ውል እያላቸው በውሉ ላይ በተቀመጡት ዝርዝሮች መሠረት ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ከዛሬ ጀምሮ እንደሚለያዩ ሥራ-አስኪያጁ...