የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ ውድድር መርሐ-ግብር ወጥቷል

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ እና ከፍተኛ ሊግ የሚሳተፉ ክለቦች ከጠዋት ጀምሮ የደንብ ውይይት ያደረጉ የሁለቱ ሊጎች የደንብ ውይይት ከተደረገ በኋላም እጣ ወጥቷል። ከደቂቃዎች በፊት የወጣው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ድልድል ያስነበብን ሲሆን አሁን ደግሞ የሁለተኛው ሊግ እጣ ወጥቷል። በዚህም በባቱ ከተማ ከታህሳስ 17 ጀምሮ በሚደረገው ውድድር ላይ በመጀመሪያ ሳምንት የተገናኙት ክለቦች የሚከተሉት ናቸው።

የአንደኛ ሳምንት መርሐ ግብር

ሀላባ ከተማ ከ ለገጣፎ ለገዳዲ
ሰበታ ከተማ ከ ንፋስ ስልክ ላፍቶ
ቂርቆስ ክ/ከተማ ከ ሀምበሪቾ ዱራሜ
አሰላ ከተማ ከ ፋሲል ከነማ
ኢ/ስ/ አካዳሚ ከ ሱሉልታ
ሲዳማ ቡና ከ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ
አራዳ ክ/ከተማ ከ ልደታ ክ/ከተማ

ያጋሩ