አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች | ሀዋሳ ከተማ ከ ሀዲያ ሆሳዕና

የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የአምስተኛ ሳምንት የመክፈቻ ጨዋታን አሁናዊ መረጃዎች በሚከተለው መልኩ አሰናድተናቸዋል።

በአራተኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ-ግብር በወልቂጤ ከተማ አንድ ለምንም የተረቱን ባለሜዳዎቹ ሀዋሳ ከተማዎች ለሁለተኛ ጊዜ ሦስት ነጥብ ለተጋጣሚ ካስረከቡበት የመጨረሻ ጨዋታቸው አራት ለውጦችን አድርገዋል። በዚህም ኤፍሬም አሻሞን በአዲስዓለም ተስፋዬ፣ አቡዱልባሲጥ ከማልን በዳዊት ታደሠ፣ ዮሐንስ ሴጌቦን በመድሃኔ ብርሃኔ እንዲሁም ሄኖክ ድልቢን በበቃሉ ገነነ ተክተዋል።

እስካሁን በሊጉ ድል ማድረግ ካልቻሉ አራት ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው ሀዲያ ሆሳዕና በበኩሉ ከአዳማ ከተማ ጋር ያለ ጎል አቻ ከተለያየበት ፍልሚያ ሳምሶን ጥላሁን፣ ባዬ ገዛኸኝ እና መላኩ ወልዴ (ቅጣት) እንዲያርፉ አድርጎ ደስታ ዋሚሾ፣ ፀጋዬ ብርሃኔ እና ፍቅረየሱስ ተ/ብርሃን በመጀመሪያ አሰላለፍ ውስጥ አካቷል።

ከጨዋታው መጀመር በፊት የሀዋሳ ከተማው አሠልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ “የቡድናችን አጨዋወት ከጊዜ ወደ ጊዜ የተሻለ ነው። ከጨዋታ ጨዋታ እያደገ መጥቷል። ዛሬ በ4-3-3 አሰላለፍ አጥቅቶ ለመጫወት ነው የመጣነው።” የሚል ሀሳባቸውን ሲሰጡ የሀዲያ ሆሳዕናው ምክትል አሠልጣኝ ያሬድ ገመቹ ደግሞ “እንደወትሮው ሁሉ ለሌሎች ቡድኖች የምናደርገውን ዝግጅት ነው ዛሬም ያደረግነው። በቀላሉ እናሸንፋለን ብዬ አላስብም። ሜዳ ላይ ግን የምናየው ይሆናል።” የሚል አስተያየታቸውን ለሱፐር ስፖርት ሰጥተዋል።

ይህንን ጨዋታ ፌዴራል ዋና ዳኛ አዳነ ወርቁ የሚመሩት ሲሆን ቡድኖቹም ተከታዮቹን ተጫዋቾች በመጀመሪያ አሰላለፋቸው ውስጥ አካተው ጨዋታው የሚጀምሩ ይሆናል።

ሀዋሳ ከተማ

77 መሐመድ ሙንታሪ
7 ዳንኤል ደርቤ
26 ላውረንስ ላርቴ
5 ፀጋሰው ድማሙ
6 አዲስዓለም ተስፋዬ
18 ዳዊት ታደሠ
14 መድሃኔ ብርሃኔ
8 በቃሉ ገነነ
29 ወንድማገኝ ኃይሉ
17 ብሩክ በየነ
10 መስፍን ታፈሰ

ሀዲያ ሆሳዕና

1 ሶሆሆ ሜንሳህ
5 ቃለአብ ውብሸት
12 ብርሀኑ በቀለ
16 ፍሬዘር ካሳ
10 ፍቅረየሱስ ተ/ብርሃን
14 ኢያሱ ታምሩ
21 ተስፋዬ አለባቸው
27 አበባየሁ ዮሐንስ
29 ደስታ ዋሚሾ
4 ፀጋዬ ብርሃኔ
31 ዑመድ ዑኩሪ