የዕለቱን የመጀመሪያ ጨዋታ የተመለከቱ አሁናዊ መረጃዎች በሚከተለው ዘገባችን አጠናክረናቸዋል።
በማማዱ ሲዲቤ ሐት-ሪክ ታግዘው ጅማ አባጅፋርን በአራተኛ ሳምንት ያሸነፉት ድሬዳዋ ከተማዎች የዓመቱ ሁለተኛ ድላቸውን ካሳኩበት ጨዋታ አንድም ለውጥ ሳያደርጉ ወደ ሜዳ ገብተዋል።
በአሠልጣኝ ጻውሎስ ጌታቸው የሚመሩት ወልቂጤ ከተማዎች ደግሞ የመጀመሪያ ሦስት ነጥባቸውን ካሳኩበት የሀዋሳው ጨዋታ በቅጣት ምክንያት ከጨዋታ ውጪ የሆነውን ሙሉጌታ ወልደጊዮርጊስን ብቻ በአብርሃም ታምራት ለውጠዋል።
አሸንፈው መምጣታችው የተሻለ በተነሳሽነት እንዲጫወት እንደሚያደርጋቸው የገለፁት አሰልጣን ዘማርያም መሪዎቹ ቡድኖች ነጥብ ስለጣሉ ለማሸነፍ ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ተናግረዋል። የወልቂጤው አሰልጣኝ ጳውሎስ የዛሬውን ጨዋታ አጥቅተው እንደሚጫወቱ እና ክፍት እንደሚሆን እንዲሁም ቶሎ ቶሎ ወደ ጎል በመድረሽ እንደሚጫወቱ ገልፀዋል።
ይህንን ጨዋታ ፌዴራል ዋና ዳኛ ብርሃኑ መኩሪያ በአልቢትርነት የሚመሩት ይሆናል። ተከታታይ ድል ለማግኘት ወደ ሜዳ የሚገቡት ሁለቱ ቡድኖችም በመጀመሪያ አሰላለፍ ያካተቷቸው ተጫዋቾች ዝርዝር የሚከተለው ነው።
ድሬዳዋ ከተማ
30 ፍሬው ጌታሁን
2 እንየው ካሳሁን
13 መሳይ ጳውሎስ
20 መሐመድ አብዱለጢፍ
4 ሄኖክ ኢሳይያስ
16 ብሩክ ቃልቦሬ
5 ዳንኤል ደምሴ
19 ሙኸዲን ሙሳ
15 አውዱ ናፊዩ
9 ጋዲሳ መብራቴ
25 ማማዱ ሲዲቤ
ወልቂጤ ከተማ
1 ሲልቪያን ህቦሆ
12 ተስፋዬ ነጋሽ
19 ዳግም ንጉሴ
24 ውሀብ አዳምስ
3 ረመዳን የሱፍ
8 በኃይሉ ተሻገር
22 አብርሐም ታምራት
14 አብዱልከሪም ወርቁ
11 እስራኤል እሸቱ
20 ያሬድ ታደሰ
9 ጌታነህ ከበደ