በሁለቱ አካላት ዙርያ የተፈጠረው ውዝግብ ወደ መደበኛ ፍርድቤት አምርቶ ጉዳያቸው በዛሬው ዕለት በችሎት ታይቷል።
ከዚህ ቀደም በነበረው ተደጋጋሚ ዘገባችን የአዲስ አበባ የቀድሞ አሰልጣኝ እስማኤል አበቡበከር እና የቡድን መሪው አቶ ሲሳይ ተረፈ መካከል የተፈጠረ ውዝግብ ወደ ኃይል አምርቶ ክለቡ የቀረበለትን ሪፖርት ከመረመረ መኃላ የተለያዩ ውሳኔዎችን ማሳለፉ ይታወቃል። ይህ በዚህ ያላቆመው የሁለቱ አካላት ጉዳይ ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት አምርቶ ክስ መመስረቱም ይታወሳል።
በዚህም መሠረት የመጀመርያ ቀጠሯቸውን አክብረው በዛሬው ዕለት በሲዳማ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍ/ችሎት በመገኘት ጉዳያቸው የታየ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ተለዋጭ ቀጠሮ ለህዳር 24 በመስጠት ሸኝቷቸዋል። እየወጡ ባሉ ዘገባዎች ከሆነ ይህ ጉዳይ እየከረረ በመሄድ ሌሎች አዳዲስ ክሶች በሁለቱም ወገን ሊከፈት እንደሚችል ሰምተናል።
በትናትንናው ምሸት አዲስ አበባ ከተማ ከአዳማ ከተማ ጋር ባደረገው ጨዋታ አሰልጣኝ እስማኤል አቡበከርም ሆነ የቡድን መሪው አቶ ሲሳይ ተረፈ በክቡር ትሪቡን በመገኘት ጨዋታውን ሲከታተሉ እንደነበረ ታዝበናል።