አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች | ባህር ዳር ከተማ ከ መከላከያ

ጥሩ ፉክክር እንደሚደረግበት የሚገመተው ጨዋታ ከመጀመሩ በፊት ያሉ አሁናዊ መረጃዎች እንደሚከተለው ተሰናድተዋል።

በወልቂጤ ከተማ ነጥብ ከተጋሩ በኋላ በአርባምንጭ ከተማ የተረቱት ባህር ዳር ከተማዎች ዳግም ወደ ደረጃ ሰንጠረዡ አናት ለመምጣት ሦስት ነጥብ ካስረከቡበት ጨዋታ ሦስት ለውጥ አድርገዋል። በዚህም የቡድኑ አሠልጣኝ አብርሃም መብራቱ በግብ በረቶቹ መሐከል አቡበከር ኑረሪን በፋሲል ገብረሚካኤል፣ ሳላምላክ ተገኘን በመናፍ ዐወል እንዲሁም ዜናው ፈረደን በዓሊ ሱሌይማን ተክተዋል።

በሦስተኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ-ግብር አስደንጋጭ ሽንፈት በአዲስ አበባ ከተማ ከገጠማቸው በኋላ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ነጥብ የተጋሩት መከላከያዎች ደግሞ ሁለት ተጫዋች ለውጠዋል። በለውጦቹም አሠልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ከቅጣት መልስ ያገኙትን ገናናው ረጋሳን ጨምሮ ሰመረ ሀፍታይን በብሩክ ሰሙ እና አለምአንተ ካሳ ለውጠዋል።\

ተሸንፈን እንደመምጣታችን በዛሬው ጨዋታ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ እንጫወታለን ያሉት አሠልጣኝ አብርሃም መከላከያም ጠንካራ ቡድን ነው ብለዋል። አሠልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ በበኩላቸው ለባህርዳር የተለየ ዝግጅት እንዳላደረጉ ጠቁመው የተለየ ነገር ካመጡ ግን የራሳቸውን አጨዋወት እንደሚተገብሩ አመላክተዋል።

ካለፉት ሁለት ጨዋታዎች አንድ አንድ ነጥን ያገኙት ባህር ዳር እና መከላከያ የሚያደርጉትን ጨዋታ ፌዴራል ዋና ዳኛ ተካልኝ ለማ በአልቢትርነት የሚመሩት ይሆናል።

ተከታዮቹ ተጫዋቾችም በሁለቱ ቡድኖች በኩል የመጀመሪያ አሰላለፍ ቦታ የተሰጣቸው ናቸው።

ባህር ዳር ከተማ

44 ፋሲል ገብረሚካኤል
16 መሳይ አገኘው
10 ፎዐድ ፈረጃ
2 ፈቱዲን ጀማል
7 ግርማ ዲሳሳ
27 አብዱልከሪን ንኪማ
25 አለልኝ አዘነ
14 ፍፁም ዓለሙ
6 መናፍ ዐወል
17 ዓሊ ሱሌይማን
13 አህመድ ረሺድ

መከላከያ

30 ክሌመንት ቦዬ
11 ዳዊት ማሞ
2 ኢብራሂም ሁሴን
4 አሌክስ ተሰማ
24 ቢኒያም በላይ
25 ኢማኑኤል ላርዬ
14 ሰመረ ሀፍታይ
5 ግሩም ሀጎስ
13 ገናናው ረጋሳ
10 አዲሱ አቱላ
18 ኡኩቱ ኢማኑኤል