አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች | ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ሲዳማ ቡና

ከሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታዎች መካከል አንዱ የሆነው ፍልሚያ ከመጀመሩ በፊት ተከታዮቹ አሁናዊ መረጃዎች እንዲህ ቀርበዋል።

በአራተኛ ሳምንት ከመከላከያ ጋር አቻ የተለያዩት ቅዱስ ጊዮርጊሶች አራት ለውጦችን በማድረግ ዛሬ ወደ ሜዳ ይገባሉ። በዚህም ሄኖክ አዱኛን በደስታ ደሙ፣ ሱሌይማን ሀሚድን በጋቶች ፓኖም፣ ቡልቻ ሹራን በተገኑ ተሾመ እንዲሁም አቤል ያለውን በኢስማኤል ኦሮ-አጎሮ ለውጠዋል።

እንደ ተጋጣሚያቸው ቅዱስ ጊዮርጊስ ሁሉ ባሳለፍነው ሳምንት አቻ የተለያዩት (ከሰበታ ከተማ) ሲዳማ ቡናዎችም ከመጨረሻ ፍልሚያቸው ሦስት ለውጦችን አከናውነዋል። በለውጦቹም ጊት ጋትኩት፣ ቴዎድሮስ ታፈሠ እና ዳዊት ተፈራ እንዲያርፉ ተደርጎ ግርማ በቀለ፣ ብሩክ ሙሉጌታ እና ብርሃኑ አሻሞ ወደ መጀመሪያ አሰላለፍ ተካተዋል።

የቅዱስ ጊዮርጊሱ ምክትል አሠልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ በቅድመ ጨዋታ አስተያየታቸው “ሁሌም እንደምናደርገው ለማሸነፍ ነው የመጣነው” ሲሉ ሲደመጡ የሲዳማ ቡናው ዋና አሠልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ደግሞ “ካለፈው ጨዋታ አንፃር የዛሬው ውጤት ካለንበት ለመውጣት አስፈላጊያችን ነው።” በማለት ተናግረዋል።

ይህንን ተጠባቂ ጨዋታ ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ በዓምላክ ተሰማ በመሐል አልቢትርነት የሚመሩት ይሆናል። ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያ አሰላለፍ ያካተቷቸው ተጫዋቾችም የሚከተሉት ናቸው።

ቅዱስ ጊዮርጊስ

30 ቻርልስ ሉክዋጎ
24 ኤድዊን ፍሪምፖንግ
4 ምኞት ደበበ
6 ደስታ ደሙ
5 ሀይደር ሸረፋ
18 ከነዓን ማርክነህ
15 ጋቶች ፓኖም
20 በረከት ወልዴ
11 አማኑኤል ገብሪካኤል
28 ኢስማኤል ኦሮ-አጎሮ
9 ተገኑ ተሾመ

ሲዳማ ቡና

30 ተክለማርያም ሻንቆ
3 አማኑኤል እንዳለ
5 ያኩቡ መሐመድ
21 ሰለሞን ሀብቴ
19 ግርማ በቀለ
16 ብርሃኑ አሻሞ
20 ሙሉዓለም መስፍን
7 ፍሬው ሰለሞን
9 ሀብታሙ ገዛኸኝ
11 ይገዙ ቦጋለ
14 ብሩክ ሙሉጌታ