በአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከጎፈሬ የትጥቅ አምራች ጋር በመሆን ለሁለት ቀናት የሚቆይ ስልጠና ሊሰጡ ነው።
የትጥቅ አምራቹ ጎፌሬ ከአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጋር አብሮ ለመስራት በደረጉት ስምምነት መሠረት የመጀመርያ ምዕራፍ ስራቸውን በአዲስ አበባ ለሚገኙ ክለቦች በሙሉ የሚገኙበት ስልጠና ነገ በቤስት ዌስተርን ሆቴል የሚሰጥ ይሆናል።
ለሁለት ቀናት የሙሉ ቀን በሚሰጠውን በዚህ ስልጠና የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ባለሙያዎች በማርኬቲንግ እና የክለብ አወቃቀር ዙርያ ላይ ያተኮረ ስልጠና እንደሚሰጥ ሰምተናል። የክለቦችን የፋይናስ አቅም ለማሳድግ ይጠቅማል ተብሎ በታሰው በዚህ ስልጠና የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን እና ጎፈሬ ይህን ስልጠና በመስጠት አብሮ ለመስራት ይጀምሩ እንጂ በቀጣይ ጊዜያት በተለያዩ የከተማዋን እግርኳሱ በሚያሳድጉ ጉዳዮች ዙርያ ሰፊ ስራ እንደሚሰሩ ሰምተናል።