ከሜዳው ውጭ ባሉ ጉዳዮች የተለያዩ ውሳኔዎች እየተላለፈበት የሚገኘው ሀዲያ ሆሳህና የዕግድ ውሳኔ ተላልፎበታል።
ከዚህ ቀደም አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለን አስመልክቶ በዲሲፕሊን ኮሚቴ የተወሰነው ውሳኔ ተገቢ አይደለም በማለት ይግባኝ የጠየቀው ሀዲያ ሆሳዕና በይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ውሳኔው ፀንቶበት ክለቡ ከሚያዚያ ወር ጀምሮ ያልከፈለውን ደሞዝ ለአሰልጣኙ እንዲከፍል ቀነ ገደብ ተቀምጦለት ውሳኔ ማሳለፉ ይታወቃል።
ሆኖም በተሰጠው ቀነ ገደብ መሠረት ክፍያው ተግባራዊ አልተደረገም ሲሉ የአሰልጣኙ ወኪልና የሕግ አማካሪ ጠበቃ አቶ ብርሃኑ በጋሻው ባቀረቡት አቤቱታ መሠረት በዛሬው ዕለት ፌዴሬሽኑ በቀጣይ የተጫዋቾች ዝውውር መስኮት ጀምሮ ክለቡ የታገደ መሆኑን በደብዳቤ አሳውቋል።