ባለፈው ሳምንት በወጣው እጣ ስነስርዓት ላይ በክፍያ ምክንያት ያልተገኙ ሰባት ክለቦች በዛሬው ዕለት ምድባቸውን አውቀዋል።
በፌዴሬሽኑ ፅህፈት ቤት በተከናወነው ስነስርዓት ላይ ሰባቱም ክለቦች (ጋሞ ጨንቻ፣ ነገሌ አርሲ፣ ካምባታ ሺንሺቾ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ፣ ወላይታ ሶዶ ከተማ፣ ጅማ አባ ቡና እና አቃቂ ቃሊቲ) የተገኙ ሲሆን ከዚህ ቀደም እድባቸውን ያወቁት መድን እና ባንክም በታዛቢነት ተገኝተዋል።
በወጣው ዕጣ መሠረት በምድብ ሀ ጋሞ ጨንቻ እና ነገሌ አርሲ፣ በምድብ ለ ሺንሺቾ እና ኮልፌ፣ በምድብ ሦስት ሶዶ ከተማ፥ ጅማ አባ ቡና እና አቃቂ ቃሊቲ ተደልድለዋል።
የውድድሩ ሙሉ የምድብ ድልድል ይህንን ይመስላል፦
ምድብ ሀ
ገላን ከተማ
አምቦ ከተማ
ኢትዮ ኤሌክትሪክ
ሻሸመኔ ከተማ
ሀላባ ከተማ
ጌዲዮ ዲላ
ባቱ ከተማ
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ጋሞ ጨንቻ
ነገሌ አርሲ
ምድብ ለ
ስልጤ ወራቤ
ለገጣፎ ለገዳዲ
ቡታጅራ ከተማ
ካፋ ቡና
ቤንች ማጂ ቡና
ቡራዩ ከተማ
ቂርቆስ ክ/ከተማ
ሰንዳፋ በኬ ከተማ
ካምባታ ሺንሺቾ
ኮልፌ ቀራኒዮ
ምድብ ሐ
ሀምበሪቾ ዱራሜ
ፌዴራል ፖሊስ
ኢትዮጵያ መድን
ነቀምት ከተማ
ጉለሌ ክ/ከተማ
የካ ክፍለ ከተማ
ደቡብ ፖሊስ
ወላይታ ሶዶ ከተማ
ጅማ አባ ቡና
አቃቂ ቃሊቲ
ከእጣ ማውጣቱ በመቀጠል ውድድሩ ላይ የሚሳተፉ ክለቦች የሚጠበቅባቸውን ክፍያ እንዳልከፈሉ ከተረጋገጠ የመጀመርያ ጨዋታቸው ፍርፌ እንደሚሰጥባቸው የተገለፀ ሲሆን ውድድሩን ከሚያስተናግዱ ክለቦች አንዱ የሆነው ሀዋሳ ከተማ ማከናወን እንደማይችል በማሳወቁ ሌላ አማራጭ ከተማ እንደሚፈለግ ተገልጿል።