ለ2022 ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ዓለም ዋንጫ ለማለፍ በሦስተኛ ዙር ማጣርያ ቦትስዋናን የሚገጥመው የሴቶች ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አሰላለፍ ታውቋል።
በኮስታሪካ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ሩዋንዳን በድምር ውጤት አሸንፎ ወደ ሦስተኛው የማጣርያ ዙር ያለፈው የወቅቱ የሴካፋ ቻምፒዮን በዛሬው ዕለት የዙሩን የመጀመርያ ጨዋታ በፍራንሲስ ታውን በሚገኘው ኦቤድ ቺሉሚ ስታዲየም ያከናውናል። ምሽት 1 ሰዓት ለሚደረገው ጨዋታም ዋና አሰልጣኙ ፍሬው ኃይለገብርኤል የመጀመርያ አሰላለፋቸውን መምረጣቸውን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል።
ግብ ጠባቂ
እየሩሳሌም ሎራቶ
ተከላካዮች
ናርዶስ ጌትነት
ብርቄ አማረ
ቤተልሔም በቀለ
ብዙዓየሁ ታደሰ
አማካዮች
ኝቦኝ የን
ገነት ኃይሉ
መሳይ ተመስገን
አጥቂዎች
ቱሪስት ለማ
ረድኤት አስረሳኸኝ
አርየት ኦዶንግ