ያለ ግብ በአቻ ውጤት ከተጠናቀቀው የስድስተኛ ሳምንት የመክፈቻ ጨዋታ በኃላ የሁለቱ ቡድኖች አሸልጣኞች ተከታዩን አስተያየት ሰጥተዋል።
ዘማርያም ወ/ጊዮርጊስ – ድሬዳዋ ከተማ
ስለ ዕለቱ የቡድኑ እንቅስቃሴ
“ሁለታችንም ተሸንፈን እንደመምጣታችን ፈተና እንደሚገጥመን አስበን ነበር ፤ እድሎችን መፍጠር ብንችልም አሁንም አጨራረስ ላይ ክፍተቶች አሉብን። ይህም በኃላ ላይ የሚያስቆጩን ይመስለኛል። አጨራረሳችን የማናስተካክል ከሆነ ረጅም ርቀት ለመጓዝ እንቸገራለን።”
ከጨዋታው በፊት ያቀዱትን ማሳካት ስለመቻላቸው
“ሙሉ ለሙሉ ባይሆንም ማየት ችለናል ወደፊት እንሄዳለን ኳሶችን ከመስመር ወደ ጎል እናደርሳለን ግን አጨራረስ ላይ ግን ክፍተቶች አሉብን ይሀንንም በግልፅ ተነጋግረን ቀርፈን መምጣት ይኖርብናል አንዳንድ ቢድኖች ከአንድ አንድ እድል አግኝተን ያስቆጥራሉ እኛ ግን ተደጋጋሚ እድሎችን ፈጥረን መጠቀም እየቻልን አይደለም።
ዘላለም ሽፈራው – ሰበታ ከተማ
ስለጨዋታ መንገዳቸው እና ውጤቱ
“በጨዋታው ከጥንቃቄ ባለፈ ባለፉት ጨዋታዎች ነጥብ አለመያዛችን ተጫዋቾች ላይ ያለመረጋጋት እና ጭንቀት እንዳለ ይታያል ስለዚህ በተወሰነ መልኩ ውጤቱ ይገልፀዋል።”
ሜዳ ላይ ተጫዋቾቹ ስላሳዩት ትጋት
“የመጀመሪያ ሀሳባችን የነበረው የምንነጥቀው ኳሶችን ተጠቅመን የመልሶ ማጥቃቶችን መሰንዘር ነበር ለዚህም በራሳችን የመከላከል ወረዳ የምንነጥቀውን ኳስ በፍጥነት ተጋጣሚ ሳጥን በማድረስ አማካዮቻችን የአጥቂውን ቁጥር መጨመር አልቻሉም በዚህ ልክ ግን መንቀሳቀስ አልቻልንም።”
በሁለተኛ አጋማሽ ተነጋግረው ስለገቡት ሀሳብ
“በመስመር ጨዋታ ብልጫ አንደሚኖር አስቀድመን ተነጋግረን ነበር ይህን ለማቆም ነጋግረን ነበር ነገርግን አፈፃፀማችን በዚያ ልክ አልነበረም።በእረፍት ሰአትም የተነጋገርነው ይህን መቀነስ ካሎቻልን ዋን እንደምንከፍል ነው ይህም በተወሰነ መልኩ በሁለተኛው አጋማሽ አድርገነዋል።”