የአሰልጣኞች አስተያየት | ኢትዮጵያ ቡና 1-0 መከላከያ

የስድስተኛ ሳምንት የቀን የመጨረሻ ጨዋት ኢትዮጵያ ቡና መከላከያን ከረታበት ጨዋታ መልስ አሰልጣኞቹ ለሱፐር ስፖርት ሀሳባቸውን አጋርተዋል።

አሰልጣኝ ካሣዬ አራጌ – ኢትዮጵያ ቡና

እንቅስቃሴው ባሰቡት መልኩ ስለመሄዱ

ከባለፈው ጨዋታ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ነገር ቡድናችን ላይ ይታይ ነበረ። ያው በማሸነፍ ደረጃ ተሳክቶልናል። ከእረፍት በኃላ ጫና ሊኖርብን እንደሚችል አስበናል። ያንን ጫና ኳሱን በመቆጣጠር ማራቅ ነበር። ያንን በተገቢው መንገድ አልሰራንም። ግን ከእረፍት በፊት የነበረው ነገር ጥሩ ነበር።

በሁለተኛው አጋማሽ በማጥቃቱ በኩል ስለነበረው ድክመት

ከመከላከያ ብዙ የሚጣሉ ኳሶች ነበሩ። እነዚህ ኳሶች ይዘን ወደ ተቃራኒ ሜዳ ስንገባ በቁጥር አንሰን ስለምንገባ መከላከያ በቀላሉ እየተነጠቅን ያገኙታል ተመልሱ ይመጣል ድግግሞሽ ነበር። ምክንያቱም ኳሶች በሚጣሉበት ጊዜ የኛ ልጆች ወደ ኃላ ይገባሉ። ምክንያቱም የእነርሱ ብዙ ቁጥር እኛ ሜዳ ኳስ ለማስጣል ይገቡ ስለነበረ እኛ ደግሞ ያስጣልነውን ኳስ በቁጥር አንሰን ስለምንገባ ያ ይመስለኛል እኛ ጋር የነበረው ድክመት።

ስለ ዊልያም ሰለሞን

እዛ መሀል ላይ ያሉ ልጆች ሁልጊዜ የሚጠበቅባቸው ነገር አለ። በመሠረቱ መሐል ያሉ ልጆች ብቻ አይደለም ሌሎቹም ጭምር ሂደቱን የማስቀጠል ስራ ይጠበቅባቸዋል። ሌላው መሐል ላይ የሚጫወቱ በቀኝ እና በግራ የሰጠናቸው ሥራ ነበር። ፊት ላይ ከሚጫወቱ ተጫዋቾች ጀርባ የሚከፈት ቦታ ነበር። ያንን ቦታ እንዲጠቀሙበት ነበር። ከእረፍት በፊት ጥሩ ነበር። በተለይ የመጨረሻው ደቂቃ ያንን ቦታ እየተጠቀሙበት ነበር የእኛ ልጆች ከእረፍት በኃላ ብዙ አልነበረም። ያው በግሉ አቅም ያለው ልጅ ስለነበረ እስከ ዛሬ በነበሩ ጨዋታዎች አቅሙ እየታየ ነው። ያው ቡድን ውስጥ የሚሰጣቸው ሚና ነው ለእርሱ የሚሰጠው።

ግብጠባቂው በረከት ሲገባ የተነጋገሩት ነገር ካለ

የተነጋገርነው ነገር አልነበረም። ቀጥታ ፍፁም ቅጣት ምት ከተገኘ በኃላ ነው የገባው ለማዳን ነው የገባው። ሌላ የተነጋገርነው ሌላ ሰው ስለማስወጣት እና በአስር በመሆን የሚፈጠረውን ክፍተት እንዴት መቆጣጠር እንደሚገባ ነው የተነጋገርነው ከበረከት ጋር የተነጋገርነው የለም የራሱን ብቃት ተጠቅሞ ያዳነው ነው።

በተከታታይ ጨዋታ ስለማሸነፋቸው

ማሸነፋችን ጥሩ ነው ከስነ ልቦና አንፃር ትልቅ ጠቀሜታ አለው። ግን ሁሌ ማሸነፍን ጠብቀን የምንሄድበት ከባለፈው ጨዋታ ተነስተን የተበጋገርንበት ነበር። እርሱን በመንፈልገው ደረጃ እየሄደ አይደለም። አርመን መምጣት አለብን። ማሸነፋችን ግን በጣም ጥሩ ነው።

አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ – መከላከያ

ስለ ጨዋታው

ጨዋታው ከውጤት ጋር ከተገናኘ ተሸንፈናል። ከዛ ውጭ ከእረፍት በፊት በምንፈልገው መልኩ አልተጫወትንም። በጣም አፈግፍገው ነበር። ግን የፈለግነው እንደዛ አልነበረም ተጭነን መጫወት ነበር። ከእረፍት በኃላ የተሻለ ነገር አድርገን መጫንም ችለን ሙከራዎች አድርገና ፍፁም ቅጣት ምት አግኝተን ነበር። የእግርኳስ አንዱ ጠባይ ይህ ነው።

የመጀመርያው አጋማሽ የማጥቃት መንገዳቸው መሀል ላይ መሆኑ

የመጀመርያው አጋማሽ እንደፈለግነው አልተጫወትንም። አዲስ የምንሞክረው ተጫዋች ነበር። ያንን ስራውን አልሰራም። አጥቅተን መጫወት ነበር የምንፈልገው ቡድኑ አፈገፈገ። በኃላ መክረን ገብተን አጋጣሚ አግኝተን ነበር። ያገኘነውን አልተጠቀምንም።

ስለ ፍፁም ቅጣት ምቱ

ያው ወይ ታገባለህ አልያም ትስታለህ ከሁለቱ አንዱ ነው የሚሆነው። አንዱ ጥሩ ተጫዋቻችን ነው የሳተው። ይህ ደግሞ የጨዋታው አንዱ ጠባይ ነው። ግብጠባቂውም ስራው ነው። ሁልጊዜ ያገኘ ያገባል ብለህ አታምንም። ግብጠባቂው በገባበት ደቂቃ ጥሩ ነገር ሰርቷል። ቡናዎች ያገኙትን ውጤት አስጠብቀው ወጥተዋል።

ወደ ተሻለ ደረጃ የሚደረሱበትን ውጤት አላማሳካታቸው የሚያሳድረው ነገር

የለም ብናገኝ ወደ ሁለተኛ ደረጃ እንሄድ ነበር። ይህ ይጠቅመናል የቢድኑን ስነ ልቦና ከፍ ለማድረግ ለቡድኑም በጣም የሚጠቅም ነው። የምንጫወተውም ለዛ ነው ግን አላገኘነውም።