ከፍተኛ ሊግ | ደቡብ ፖሊስ ስምንት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የነባሮችንም ውል አድሷል

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሐ ስር የተደለደለው ደቡብ ፖሊስ ስምንት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የአስራ አምስት ነባሮችን ውልም አራዝሟል፡፡

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በሁለት የተለያዩ ጊዜያት የመሳተፍ ዕድልን አግኘቶ የነበረው ደቡብ ፖሊስ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የምድብ ሐ ስር ተደልድሎ ዝግጅቱን ጀምሯል፡፡ ከአሰልጣኝ አላዛር መለሰ ጋር የአንድ ዓመት ቀሪ ውል ያለው ክለቡ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታውን ለማድረግ ከሰሞኑ ወደ ጅማ የሚያመራ ሲሆን ቡድኑን ጠንካራ ተፎካካሪ ለማድረግ የስምንት አዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር ሲፈፅም የአስራ አምስት ነባሮችን ውልም አራዝሟል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ክለቡ አምስት ወጣት ታዳጊዎችን ከታችኛው የቡድኑ የዕድሜ ዕርከን ማሳደግ ችሏል፡፡

ታሪኩ አረጋ (ግብ ጠባቂ ከመከላከያ ተስፋ) ፣ አቤኔዘር ቾንቤ (ተከላካይ ከጂንካ ከተማ) ፣ ዳዊት ጥላሁን (ተከላካይ ከጩኮ ከተማ) ፣ ብሩክ ዳንኤል (አማካይ ከሺንሺቾ ከተማ) ፣ ማቲዮስ መዶልቾ (አማካይ ከኮንሶ ጋርዱላ) ፣ አማኑኤል ኪሩቤል (አማካይ ከሲዳማ ቡና) ፣ ምንተስኖት ታምራት (አጥቂ ሺንሺቾ) እና ኤልያስ እንድሪያስ (አጥቂ ከጅማ አባቡና) አዳዲሶቹ የክለቡ ፈራሚዎች ናቸው፡፡