በአቻ ውጤት ከተጠናቀቀው ጨዋታ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን ሀሳብ ሰጥተዋል።
ፋሲል ተካልኝ – አዳማ ከተማ
ስለጨዋታው
“ጥሩ ጨዋታ ነበር በጨዋታው ከተጋጣሚያችን በተሻለ የማሸነፍ ፍላጎት ተጫውተናል ግን ያው ጎል እስካላገባን ድረስ ሶስት ነጥብ ማግኘት አልቻልንም። ቀላል ቀላል ግብ መሆን የሚችሉ አጋጣሚዎችን መጠቀም ስላልቻልን የምንፈልገውን ውጤት ማግኘት አልቻልንም።”
የግብ እድሎችን ወደ ግብ ለመለወጥ መስራት ስለሚገባቸው ነገር
“የመጀመሪያው ልምምዶችን መስራት ነው ሁለተኛው የተጫዋቾች ምርጫ ነው ሶስት ነጥቡን ስለፈለግን የመቻኮል ነገር ነበር በቀጣይ ሶስት ነጥቡን ለማግኘት ከፈለግን ማስተካከል ይኖርብናል።”
በዛሬው ጨዋታ ሶስት ነጥብ ስላለማግኘታቸው
“ሶስት ነጥብ ብናገኝ በሰንጠረዡ ከፍ ያደርገን ነበር ግን ያው አለተሳካም በቀጣይ ሰርተን በቀጣይ ተስፋ አደርጋለሁ ሶስት ነጥብ እናገኛለን።”
ዘሪሁን ሸንገታ -ቅዱስ ጊዮርጊስ
ስለጨዋታው
“በጨዋታው ላይ ጥሩ አልነበርንም። ባሰብነው መንገድ አልተንቀሳቀስንም። በግል የምጠቅሰው ሰው ባይኖርም እንደቡድን ግን የነበረን እንቅስቃሴ ትክክል አልነበረም።በመከላከልም በማጥቃትም የነበረው ነገር ጥሩ ስላልነበረ በጥቅሉ ቡድኑ ላይ ስራ ይፈልጋል።በቀጣይ ጨዋታ እንደ ቡድን የተነጋገርናቸው ነገሮች አሉ እነሱን አስተካክለን እንቀርባለን።”
ግብ አለማስተናገዳቸው እድለ ካስባላቸው
“በሜዳ ላይ ካሳየነው ደካማ እንቅስቃሴ አንፃር ከአዳማ ጋር ነጥብ መጋራትችን እድለኛ ያረገናል። ”