\”ቢያንስ ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ ምንም ፀፀት እንዳይኖር በግሌ ያለኝን ለመስጠት ዝግጁ ነኝ\” ጋቶች ፓኖም

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አማካይ ጋቶች ፓኖም ከዛሬው ወሳኝ ጨዋታ በፊት ያጋራንን ሀሳብ ይዘን ቀርበናል።

\"\"

ስለዝግጅቱ…

ዝግጅቱ እንዳያችሁት ነው። በጣም አሪፍ ነው። ሁሉም ተጫዋቾች በሙሉ ጤንነት ላይ ይገኛሉ። ለጨዋታዎቹም በጥሩ ሁኔታ ነው የተዘጋጀነው።

ስለተጋጣሚ ቡድን…

ጊኒ ጠንካራ ቡድን ነው። አውሮፓ የሚጫወቱ ብዙ ተጫዋቾች አሉ። ለእነርሱ የተለየ ትኩረት አናደርግም። ነገርግን ጨዋታው ወሳኝ ነው። ምክንያቱም እነርሱም እኛም ነን ጨዋታውን የምንፈልገው ፤ በአፍሪካ ዋንጫ ደግሞ በዕለቱ የምታደርገው ብቃት ነው ወሳኙ ነገር። ስለዚህ ለዚህ እንደኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዝግጁ ነን። ሁሉም ተጫዋቾችም በሚገባ ተዘጋጅተዋል።

በግልስ ከጋቶች ምን ይጠበቅ ?

በግል የሚቻለኝን አቅሜን አውጥቼ ማውጣት ነው የማስበው። ቢያንስ ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ ምንም ፀፀት እንዳይኖር በግሌ ያለኝን ለመስጠት ዝግጁ ነኝ።

በተከታታይ ወደ አፍሪካ ዋንጫው ለማለፍ ስላላቸው ጉጉት…

እንደ ተጫዋች ታሪክ ሰርተህ ስታልፍ ትደሰታለህ። በተከታታይ የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ የሚያስች ታሪክ ላይ ከጫፍ ደርሰናል። አንድ እግራችንን ለአይቮሪኮስቱ ውድድር ለማስገባት የጊነው የደርሶ መልሱ ጨዋታዎች በጣም ወሳኝ ናቸው። ለዚህ ደግሞ እኛም ራሳችንን አዘጋጅተናል።

\"\"