የዋልያዎቹ የአፍሪካ ዋንጫ ስብስብ ይፋ ሆኗል

በካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያን የሚወክሉት 25 ተጫዋቾች አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ይፋ አድርገዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከስምንት ዓመታት በኋላ ወደ አህጉራዊ ውድድር መመለሱ ይታወቃል። ከአስራ ሰባት ቀናት በኋላ በሚጀመረው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይም በምድብ አንድ ከአዘጋጇ ካሜሩን፣ ኬፕ ቨርዴ እና ቡርኪና ፋሶ ጋር መደልደሏ ይታወሳል። ለዚህ የአፍሪካ ዋንጫም ብሔራዊ ቡድኖች ለተጫዋቾች ጥሪ እያቀረቡ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ውበቱ አባተም ለ25 ተጫዋቾች ጥሪ ማቅረባቸውን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በማኅበራዊ ገፁ ይፋ አድርጓል።

ግብ ጠባቂዎች

ፋሲል ገ/ሚካኤል (ባህርዳር ከነማ)
ተ/ማሪያም ሻንቆ (ሲዳማ ቡና)
ጀማል ጣሰው (አዳማ ከነማ)

ተከላካዮች

ደስታ ዮሃንስ (አዳማ ከነማ)
አስቻለው ታመነ (ፋሲል ከነማ)
ምኞት ደበበ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
አሥራት ቱንጆ (ኢትዮጵያ ቡና)
መናፍ ሐወል (ባህር ዳር ከነማ)
ሱሌይማን ሀሚድ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ያሬድ ባየህ (ፋሲል ከነማ)
ረመዳን የሱፍ (ወልቂጤ ከነማ)

አማካዮች

በዛብህ መለዮ (ፋሲል ከነማ)
መስዑድ መሀመድ (ጅማ አባጅፋር)
አማኑኤል ዮሐንስ (ኢትዮጵያ ቡና)
ጋቶች ፓኖም (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ሽመልስ በቀለ (ኣል ጉና)
ፍሬው ሰለሞን (ሲዳማ ቡና)
ፍፁም ዓለሙ (ባህር ዳር ከነማ)

አጥቂዎች

ሽመክት ጉግሳ (ፋሲል ከነማ)
አቡበከር ናስር (ኢትዮጵያ ቡና)
ሙጂብ ቃሲም (ኣል ሞካስ)
ዳዋ ሁቴሳ (አዳማ ከነማ)
ጌታነህ ከበደ (ወልቂጤ ከነማ)
መስፍን ታፈሰ (ሀዋሳ ከነማ)
አማኑኤል ገ/ሚካኤል (ቅዱስ ጊዮርጊስ)