ብሔራዊ ቡድኑ የአቋም መለኪያ ጨዋታ ከማን ጋር እንደሚያደርግ ፍንጭ ተሰጥቷል

በኢሊሊ ሆቴል በብሔራዊ ቡድኑ የአፍሪካ ዋንጫ ጉዞ አስመልክቶ በተካሄደው ጋዜጣዊ መግላጫ ላይ ብሔራዊ ቡድኑ ከማን ጋር የአቋም መለኪያ ጨዋታ እንደሚያደርግ ተጠቁሟል።

ከኢትዮጵያ ውጭ ብሔራዊ ቡድን ዝግጅቱን ከሀገር ውጭ ሊያደርግ እንደሆነ እና በዝግጅቱ ወቅት የአቋም መለኪያ ጨዋታ ሊያደርግ እንደሚችል ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወቃል። አሁን በኤሊሊ ሆቴል የካሜሩን የአፍሪካ ዋንጫን ጉዞ አስመልክቶ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና የፌዴሬሽኑ ዋና ፀኃፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይም በያውንዴ በሚኖረው የ12 ቀናት የዝግጅት ጊዜ ውስጥ አስቀድሞ ከፊፋ ዕውቃና በተሰጠው ኤጀንት አማካኝነት ከሁለት ያላነሰ አልያም ሦስት የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ላመድረግ ሁኔታዎች መመቻቸቱን ተናግረዋል። በዚህም መሠረት ከሞሮኮ ከሱዳን እና ከዙባምቤ ሀገራት ጋር ጨዋታዎችን ለማድረግ መታሰቡን ተገልፇል።

የብሔራዊ ቡድኑ የልዑክ ቡድን ቅዳሜ ምሽት በሳካይ ላይት ሆቴል ከፍተኛ የመንግስት አካላት በተገኙበት የሽኝት መርሐግብር ከተካሄደ በኃላ በንጋታው እሁድ ወደ ሥፍራው የሚያቀኑ ይሆናል።

ያጋሩ