የአሰልጣኞች አስተያየት | ሀዋሳ ከተማ 1-0 አርባምንጭ ከተማ

ለሃምሳ ቀናት የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ከመቋረጡ አስቀድሞ የዘጠነኛው ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ በሀዋሳ ከተማ አሸናፊነት ከተጠናቀቀ በኋላ አሰልጣኞች ለሶከር ኢትዮጵያ የሰጡት አስተያየት።

አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ – ሀዋሳ ከተማ

ስለ ጨዋታው

ጨዋታው እጅግ ጠንካራ እንደሚሆን እናስብ ነበር። በዛ መንገድ ስንዘጋጅ የነበረው። ጨዋታው ጠንካራ ነበር።

ጨዋታው ረዘም ላለ ደቂቃ ያለጎል መግፋቱ በአቻ ያልቅ ይሆን የሚል ስጋት ነበረህ

ተከላካዮቻችን ስህተት ካልሰሩ እንደምናገባ ለልጆቼ እየነገርኳቸው ነበር። መልበሻ ክፍልም ስንመጣም ይህን ነግሬያቸው ነበር። ታክቲካል ዲሲፒሊን ሆናቹሁ በማይሆን መንገድ ከእናተ ስህተት ሳይመጣ እንዳይቆጠርብን ካደረግን እኛ የእነርሱን ስህተት ተጠቅመን ጎል እንደምናስቆጥር ተነጋግረን ነበር። ያን አድርገን ተከላካዮቻችን ስህተት ሳይሰሩ በጥንቃቄ አጥቂዎቻችን ጎል አስቆጥረው አሸንፈን ወጥተናል።

ስለ ብሩክ በየነ

ብሩክን ያወራነው ነገር ምድነው ለጨዋታዎች የሚሰጠው ግምት አንዳንዱን አክብዶ ነው የሚመጣው አንዳንዱን ደግሞ ቀለል አድርጎ ነው የሚመጣው በዚህ ይቸገር ነበር። አንዳንዴም አቋሙ ወጣ ገባ ይሉ የነበረው በእራሱ በሚፈጥረው ነገር ነው። በሰፊው አውርተን ዛሬ መቶ በመቶ አስተካክሎት ነው የመጣው።

እግርህ ላይ ጉዳት አጋጥሞህ ቡድን መምራት እንዴት ነው

የሚገርመው እግሬ ለሳምንት ያህል መርገጥ አይችልም ነበር። የታክቲክ ልምምዶችን የግድ እኔ መኖር ስለነበረብኝ ወንበር ላይ ቁጭ ብዬ ልምምድ አሰራ ነበር። በተመሳሳይ ሜዳ ከመጣው በኃላ ረስቼዋለው ማለት ይቻላል። አሁን ግን እየተሰማኝ ነው ማለት ይቻላል።

አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ አርባምንጭ ከተማ

ስለ ጨዋታው

ጨዋታው ጥሩ ነበር። ከመጀመርያው አጋማሽ ጀምሮ ጎል ለማስቆጠር ጥረናል ግን በፈለግነው መንገድ አልሄደም። በሁለተኛው አጋማሽ ጨዋታውን ተቆጣጥረን የጎል አጋጣሚዎችን ለመፍጠር እና ተጭኖ በመጫወት ተሳክቶልናል። በዛው ልክ ጎል ተቆጥሮብናል። ከዚህ በኃላ በእኛ ሀገረ እግርኳስ የተለመደ ነው ያገባ ይተኛል በፍጥነት ማጥቃት ደግሞ ነቅሎ የመውጣት ባህሪ አለው። አጠቃላይ ያየናቸው ጠንካራም ደካማም ጎኖች አሉ እርሱ ላይ ሰርተን እንመጣለን።

የሽንፈታቹ ምክንያት ድክመት

ያለ ምክንያት አትሸነፍም። የእነርሱ ጥረት አለ የእኛም ድክመት አለ በዚህ ምክንያት ነጥብ ጥለናል።

የሀዋሳ የዘጠኝ ሳምንት ቆይታ

ሀዋሳ ደስ የምትል ከተማ ነች፤ ሜዳ ላይ ግን ውጤቱ እንደፈለግነው አይደለም። የሚሻሻሉ ነገሮች አሉ ሠርተን እንመጣለን።

በቡድኑ ውስጥ መሻሻል ስለሚገቡ ነገሮች

ያየናቸው የምንጨምራቸው ነገሮች አሉ። በተለያዩ መልኩ አሰልጣኞቹ የምናያቸው ክፍተቶች ይኖራሉ። እነርሱ ላይ ተነጋግረን አርመን እንመጣለን።