ሽመልስ በቀለ ካሜሩን ደርሷል

የዋልያዎቹ ወሳኝ ተጫዋች ከደቂቃዎች በፊት ያውንዴ መድረሱን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

ከጥር አንድ ጀምሮ ለሚደረገው የአፍሪካ ዋንጫ ለመዘጋጀት ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ወደ ካሜሩን ያመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት ልምምዱን ሰርቷል። አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ወደ ስፍራው ይዘዋቸው ለማቅናት ካሰቧቸው 28 ተጫዋቾች መካከል ደግሞ መናፍ ዐወል በህመም ምክንያት ቀርቶ በምትኩ አህመድ ረሺድ ነገ ወደ ቦታው እንደሚያመራ ፌዴሬሽኑ ከሰዓታት በፊት ይፋ አድርጎ ነበር።

ጥሪ ከቀረበላቸው 28 ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ሽመልስ በቀለ ደግሞ ትናንት ከግብፅ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ዛሬ ረፋድ ወደ ካሜሩን እንደተጓዘ ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች። በግብፁ አል ጎውና የሚጫወተው ተጫዋቹም ቀጥር ላይ ዱዋላ የደረሰ ሲሆን ከዛም ከዱዋላ ብሔራዊ ቡድኑ ወደሚገኝበት ያውንዴ በማቅናት ከደቂቃዎች በፊት ያውንዴ እንደደረሰ ለማወቅ ችለናል።

ያጋሩ