የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን በአርባምንጭ ከተማ እያደረገ ባለው የ2014 ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ዕገዳ ላይ የነበሩትን የወ/ሮ ሶፊያ አልማሙን ዕገዳ እንዲነሳ ጉባኤተኛው በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን በአርባምንጭ ከተማ እያደረገ ባለው 13ተኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በርካታ ሀሳቦች እየተነሱ የሚገኙ ሲሆን ከፌዴሬሽኑ የስራ አስፈጻሚ ዕውቅና ውጪ በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ምርጫ ላይ በመሳተፋቸው ታግደው የቆዩ ሲሆን በዛሬው የጠቅላላ ጉባኤ ላይ ስራ አስፈፃሚው ሳይወክላቸው በኦሎምፒክ ኮሚቴ ስብሰባ ተሳትፎ በማድረጋቸው በፌዴሬሽኑ አንቀፅ 2 ቁጥር 13 መመሪያ መሠረት ታግደው የነበረ ሲሆን በጠቅላላ ጉባኤው እገዳው ይነሳል ? አልያም አይነሳም ? የሚለው ጉዳይ ላይ በፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ጂራ አማካኝነት የቀረበ ሲሆን ወ/ሮ ሶፊያም ሀሳብ እንዲሰጡ ተደርጓል፡፡
“በምርጫው ተወዳድሬ ስራዬን በተሰጠኝ ሀላፊነት ስሰራ ነበር። በተለይ የሴቶች ልማት ኮሚቴን ወክዬ በመስራት ጥሩ ውጤት አምጥቻለሁ ችግር ፈጣሪ ሰው ሆኜ አደለሁም ወደዚህ ስመጣ የሴቶችን የእግር ኳስ ተሳትፎ ለማሳደግ ነው ወደ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ያመራውት ስጠይቅም ከፕሬዚዳንቱ ጋር ተገባብተን ነበር ወደዚህ ምርጫም የገባውት ከስራ አስፈፃሚው ተቀባይነት አግኝቼ ነው፡፡ከ11 ስራ አስፈፃሚ እኔ ብቻ ነኝ ሴት ወደ ኦሎምፒክ ሳመራም የተለየ ነገር ፈልጌ አደለም። ከስራ አስፈፃሚው ፍቃድ እና ዕውቅና ሰጥቶኝ ነው የሄድኩት። ከ20 አመት በታች እዚህ የደረሰበት ስፖርቱን ያለምንም ኮሽታ ነበረ ስመራ የነበረው ይሄ ቅጣት ለእኔ አይገባኝም እግር ኳስን ለመጉዳት አይደለም እኔ የተነሳሁት። ጉባኤተኛው ይሄንን ቢረዳልኝ እና እገዳውን ቢያነሳልኝ”በማለት ተናግረዋል።
ከወ/ሮ ሶፍያ ንግግር በኋላም ፕሬዝዳንቱ አቶ ኢሳይያስ ጂራ ለጉባኤተኛው የውሳኔ ሀሳብ አቅርበው በሙሉ ድምፅ ፀድቆ እገዳው ተነስቶላቸዋል፡፡