አቶ አበበ ገላጋይ የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን ተመርጠዋል

በአርባምንጭ ከተማ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን በተጓደለው የምክትል ፕሬዝዳንት ቦታ ላይ አቶ አበበ ገላጋይ ሲመረጡ የዲሲፕሊን ኮሚቴ አባልም ተመርጧል፡፡

13ተኛው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን እያደረገ የሚገኝ ሲሆን ከፀጥታ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም የፌድሬሽኑ ምክትል ፕሬዝዳንት በሆኑት እና አሁን በቦታው በሌሉት ኮሮኔል አወል አብዱራሂም ቦታ ላይ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት እና በአሁኑ ሰአትም ዋልያዎቹን በቡድን መሪነት እያገለገሉ የሚገኙት አቶ አበበ ገላጋይ ቦታውን ለቀጣዮቹ ስድስት ወራት ማለትም የፌድሬሽኑ የምርጫ ጉባኤ እስኪከናወን ድረስ ቦታውን እንዲመሩ በአብላጫ ድምፅ በጉባኤተኞቹ ተመርጠዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ አቶ ዮሴፍ ካሳ የፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ሰብሳቢ በመሆንም ተመርጠዋል፡፡

ያጋሩ