በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወጥ አቋም ማሳየት ያልቻለው ድሬደዋ ከተማ በዛሬው ዕለት አሰልጣኙን በመገምገም የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
የድሬዳዋ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የቡድኑ የአሰልጣኝ አባላት በተገኙበት ዛሬ ረጅም ሰዓት የፈጀ እና በዘጠኝ ሳምንታት ውስጥ የቡድኑ ጠንካራ እንዲሁም ደካማ ጎን ምን ይመስል እንደነበረ ጥልቅ ግምገማ ተደርጓል። በግምገማው በርከት ያሉ አስገራሚ ጉዳዮች የተነሱ ሲሆን በዋናነት ደግሞ በዋና አሠልጣኙ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ላይ የአሠልጣኝነት ብቃት ላይ ጥያቄዎች ተነስተው ቦርዱ ውሳኔ ማሳለፉን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።
በዚህም መሠረት ከዚህ በኋላ በሚኖሩ ቀሪ ጨዋታዎች የክለቡ ዋና አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ የክለቡን የውጤት ችግር ይቀረፋል ብሎ ቦርዱ የማያምን መሆኑን በመግለፅ አሰልጣኝ ዘማርያም ታግደው እንዲቆዩ ከውሳኔ ላይ ተደርሷል።
ሶከር ኢትዮጵያ በክለቡ እና በአሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ዙርያ የሚኖሩ አዳዲስ ነገሮችን ተከታትለን እናቀርባለን።