ሀዲያ ሆሳዕና በአንድ ተጫዋች ጉዳይ የፍርድ ቤት ውሳኔ ተላለፈበት

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከተጫዋቾች ጋር በተያያዘ የተለያዩ ክሶች ሲሰሙበት የቆየው ሀዲያ ሆሳዕና የፍርድ ቤት ውሳኔ ተወስኖበታል።

የቀድሞ ተጫዋቹ አብዱልሰመድ ዓሊ ”የማትጊያ አምስት መቶ ሰማንያ ሺህ ብር በቼክ ቢሰጠኝም የሀዲያ ሆሳዕና እግርኳስ ክለብ ሊከፍለኝ አልቻለም።” በማለት በ2013 መጋቢት ወር ላይ በአቶ ብርሐኑ በጋሻው የሕግ አማካሪ ጠበቃ እና የአግር ኳስ ስፖርትኞች ሕጋዊ ወኪል አማካኝነት በመደበኛ ፍርድ ቤት ክስ ተመስርቷል።

ተከሳሽ ሀዲያ ሆሳዕና እግርኳስ ክለብ ምላሽ እንዲሰጥ በፍርድ ቤት በኩል በተለያዩ መንገዶች የቀጠሮ ቀን ጥሪ ቢደረግላቸውም መገኘት ባለመቻላቸው ሐምሌ ወር 2013 በዋላው ችሎት ውሳኔ ክለቡ ለተጫዋቹ ከላይ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን እንዲከፍል ውሳኔ አሳልፎበታል።

ሆኖም ክለቡ የተወሰነውን ውሳኔ ተግባራዊ አለማድረጉን ተከትሎ በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ካምፓኒ ሀዲያ ሆሳዕና ከሚያገኘው ገቢ በመቁረጥ በአምስት ቀናት ውስጥ ተፈፃሚ እንዲያደርግ ፍርድ ቤቱ ወስኗል።