​አሠልጣኝ ፍሬው ኃይለ ገብርኤል ለ28 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርበዋል

በጥር ወር አጋማሽ ከታንዛኒያ ጋር ወሳኝ ጨዋታ ማድረግ የሚጀምረው የኢትዮጵያ ሴቶች ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለተጫዋቾች ጥሪ አቅርቧል።

በኮስታሪካ አስተናጋጅነት ለሚከናወነው የዓለም ሴቶች ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ ውድድር ላይ ለመሳተፍ በአሠልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በማጣሪያ ጨዋታዎች አዎንታዊ ውጤት አምጥቶ ሁለት የደርሶ መልስ ጨዋታ ብቻ እንደቀረው ይታወቃል። የቡድኑ አሠልጣኝም ከፊታቸው ለሚጠብቃቸው ለታንዛኒያ ወሳኝ ጨዋታ ትናንት ምሽት ለ28 ተጫዋቾች ጥሪ ማስተላለፋቸውን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል።

ግብ ጠባቂዎች

እየሩሳሌም ሎራቶ፣ ገነት ኤርምያስ፣ ባንቺዓየሁ ደመላሽ

ተከላካዮች

ናርዶስ ጌትነት፣ ብዙዓየሁ ታደሰ፣ ትዕግስት ኃይሌ፣ ብርቄ አማረ፣ መስከረም ኢሳይያስ፣ ነፃነት ፀጋዬ፣ ቤተልሔም በቀለ፣ አይናለም አደራ፣ ባንቺይርጋ ተስፋዬ፣ ንግስት አስረስ፣ ሰናይት ሸጎ፣ ንጋት ጌታቸው፣ ማክዳ ዓሊ

አማካዮች

ኝቦኝ የን፣  መዓድን ሣህሉ፣  ገነት ኃይሉ፣ እፀገነት ግርማ፣ ቅድስት ቴቃ፣ መሳይ ተመስገን 

አጥቂዎች

አርየት ኦዶንግ፣ አረጋሽ ካልሳ ፣ ቤተልሔም ታምሩ፣ ቱሪስት ለማ፣ ረድኤት አስረሳኸኝ፣ ንግስት በቀለ

ስማቸው የተጠቀሱት ተጫዋቾችም በዛሬው ዕለት (10:00) ሲ ኤም ሲ አካባቢ በሚገኘው የካፍ የልህቀት ማዕከል ሪፖርት እንዲያቀርቡ ተመላክቷል።