
ሦስት ወሳኝ ተጫዋቾች ዋልያውን ዛሬ አያገለግሉም
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከኬፕ ቨርድ አቻው ጋር ዛሬ ምሽት ጭጫታ ሲያደርግ ሦስት ተጫዋቾች በጉዳት ምክንያት ከስብስቡ ውጪ ሆነዋል።
ድረ-ገፃችን በትናንትናው ዕለት ባስነበበችው ዘገባ ሽመልስ በቀለ እና ዳዋ ሁቴሳ የጠንቻ እና የቁርጭምጭሚት ጉዳት በማስተናገዳቸው በዛሬው ጨዋታ ላይሰለፉ ይችላሉ ብላ ነበር። አሁን ከስፍራው ባገኘነው መረጃ መሠረትም ሁለቱም ተጫዋቾች ለጨዋታው ብቁ ባለመሆናቸው ከፍልሚያው ሙሉ ለሙሉ ወጥተዋል።
ከሽመልስ እና ዳዋ በተጨማሪም በመጨረሻዎቹ ልምምድ ላይ መጠነኛ የትከሻ ጉዳት እንዳጋጠመው የሰማነው የግብ ዘቡ ፋሲል ገብረሚካኤልም ህመሙ ለክፉ የሚሰጥ ባይሆንም ለጨዋታ ስለማያደርሰው ከዛሬው ጨዋታ ውጪ እንደሆነ ሰምተናል።
ተዛማጅ ፅሁፎች
የሴቶች ፕሪምየር ሊግ | መከላከያ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሀዋሳ ወሳኝ ድል አሳክተዋል
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ17ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ በተደረጉ አራት መርሐግብሮች ጅምሩን ሲያደርግ መከላከያ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሀዋሳ ተጋጣሚዎቻቸውን...
የአሰልጣኞች አስተያየት | አዳማ ከተማ 1-1 ድሬዳዋ ከተማ
በሊጉ ለመቆየት ብርቱ ትግል ተደርጎበት ነጥብ በመጋራት ከተጠናቀቀው ጨዋታ ፍፃሜ በኋላ አሰልጣኞች የድህረ-ጨዋታ አስተያየት ሰንዝረዋል፡፡ አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ - አዳማ...
ከ17 እና ከ15 ዓመት በታች ውድድሮች የሚደረጉበት ቦታ እና ቀን ይፋ ሆኗል
የ2014 ከ17 ዓመት በታች እና ከ15 ዓመት በታች የፓይለት ፕሮጀክት ውድድሮች የሚደረጉበት ከተማ እና ቀን ታውቋል፡፡ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን...
የአዲስ አበባ ከተማ የቡድን አባላት ዝርፊያ ተፈፀመባቸው
በሲዳማ ቡና ሽንፈት ያስተናገድው የአዲስ አበባ ከተማ የቡድን አባላት ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ ዝርፊያ እንደተፈፀመባቸው ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች። ረፋድ ላይ በ29ኛ...
የሴቶች ፕሪምየር ሊግ | የሊጉ መሪ ንግድ ባንክ እና ተከታዩ ኤሌክትሪክ ሲያሸንፉ ሀዋሳ እና መከላከያ ነጥብ ተጋርተዋል
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ በአዳማ ሲከወኑ ሊጉን እየመራ የሚገኘው ንግድ ባንክ በግብ ሲንበሸበሽ ተከታዩ ኢትዮ ኤሌክትሪክ...
አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ ቅጣት ተላለፈባቸው
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንትን ተከትሎ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ተወስነዋል። ሊጠናቀቅ የሁለት ሳምንት ዕድሜ የቀረው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...