​ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊው ዋልያውን አበረታተዋል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከማድረጉ በፊት የባህል እና ስፖርት ሚኒስትሩ ቡድኑን አነቃቅተዋል።

33ኛው የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ ውድድር በ24 ተሳታፊዎች መካከል ሊደረግ የሰዓታት እድሜ ብቻ ቀርቶታል። ብሔራዊ ቡድናችንም የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታውን ከኬፕ ቨርድ አቻው ጋር ምሽት አራት ሰዓት ላይ በኦልምቤ ስታዲየም ያከናውናል። በጁዩጋ ፓላስ ሆቴል ማረፊያቸውን አድርገው የጨዋታውን መጀመር እየተጠባበቁ የሚገኙት የቡድኑ ተጫዋቾች እና የአሠልጣኝ ቡድን አባላትም በኢትዮጵያ ባህል እና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ቀጀላ መርዳሳ የማበረታቻ ንግግር እንደተደረገላቸው አውቀናል።

ክቡር ሚኒስትሩ በበይነመረብ አማካኝነት በዙም ከቡድኑ ጋር ቆይታ ሲያደርጉም መልካም ዕድል እንዲገጥማቸው ተመኝተው ተጫዋቾች እና አሠልጣኞች ሀገራቸውን እንዲያስጠሩ አደራ ብለዋል። በአሁኑ ሰዓትም የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያያይ ጂራ በተጨማሪነት ቡድኑን ለማበረታታት ስብስቡ ያረፈበት ሆቴል እንደደረሱ አውቀናል።

ያጋሩ