የፋሲል ከነማ የጎዳና ላይ ሩጫ ዛሬ ተካሄደ

ዐፄዎቹ በዛሬው እለት እስከ 10 ሺህ ሯጮች የተሳተፉበት የጎዳና ላይ ሩጫ በደመቀ አካሂደዋል።

ፋሲል ከነማን በገቢ ለማጠናከር ከሚዘጋጁ የገቢ ማስገኛ ዝግጅቶች አንዱ የሆነው እና በየዓመቱ የሚዘጋጀው የጎዳና ላይ ሩጫ የዘንድሮው መርሀ ግብር ለአራተኛ ጊዜ የተከናወነ ሲሆን ”ለአሸናፊዎቹ እሮጣለሁ” በሚል መሪ ቃል የተደረገው ሩጫው መነሻውን ማራኪ ፕላዛ ሆቴል አድርጎ መስቀል አደባባይ መጠናቀቂያውን አድርጓል፡፡

የፋሲል ከነማ ፕሬዝዳንት እና የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ዘውዱ ማለደ ፣ የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ጣሂር ኢብራሂም እና ሌሎች ከፍተና የስራ ኃላፊእኦች የተገኙበት ይህ መርሐ ግብርን ያስጀመሩት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው አቶ ዘውዱ ”ከፋሲል ከነማ ጋር ሁልጊዜ የጥር ወርን በጥምቀት እንደምቃለን” ብለዋል፡፡

በውድድሩም ከ10 ሺ በላይ ተሳታፊዎች እንደተካፈሉበት የደጋፊ ማህበሩ ሊቀመንበር አቶ ደመላሽ አበበ የገለፁ ሲሆን በወንዶች ሀብታሙ ብርሀኑ በሴቶች ደግሞ ሳምራዊት ይርጋ በአሸናፊነት እንዳጠናቀቁ የክለቡ የፌስቡክ ገፅ አስታውቋል።

 

ያጋሩ