ያውንዴ የሚገኘው የካፍ ቴክኒክ ጥናት ቡድን በምድብ ሀ ከተሳተፉ ሀምሳ ሰባት ተጫዋቾች መካከል አማኑኤል ዮሐንስን በምርጥ ቡድን ምርጫ ውስጥ አካተውታል።
ኢትዮጵያ ከቡርኪናፋሶ ጋር ነጥብ በተጋራችበት ጨዋታ ኮከብ በመባል የተመረጠው አማኑኤል ዮሐንስ በድጋሚ ለሌላ ምርጫ ውስጥ በእጩነት መካተቱን ከሰሞኑን መዘገባችን ይታወቃል። በያውንዴ ከተማ የሚገኘው የካፍ ቴክኒክ ጥናት ቡድን በምድብ ሀ በሚገኙትካሜሩን ቡርኪናፋሶ፣ ኬፕ ቨርድ እና ኢትዮጵያ እርስ በእርስ በተገናኙበት ሦስት ጨዋታዎች የተሳተፉ ሀምሳ ሰባት ተጫዋቾችን የተለያዩ መስፈርቶችን በማውጣት ከገመገመ በኃላ ምርጥ አስራ አንዱን እና የተጠባባቂ ተጫዋቾችን ምርጫ ይፋ አድርጓል።
በዚህ መሰረት የካፍ ቴክኒክ ጥናት ቡድን በአማካይ ስፍራ በሁሉም መመዘኛ የተሻለ አቋም አሳይቷል ያሉት አማኑኤል ዮሐንስን በአማካይ ስፍራ ላይ በምርጥ አስራ አንድ ውስጥ አካተውታል። በተጨማሪም በወጣቶች ዘርፍ አበቡበከር ናስር በተጠባባቂነት መካተቱን አውቀናል።
የምድብ ሀ ምርጥ አስራ አንድ ተመራጮች ዝርዝር
ግብ ጠባቂ
አንድሬ ኦናና (ካሜሩን)
ተከላካዮች
አይሳ ካቦሬ (ቡርኪና ፋሶ)
ቶሎ ንዶሆ (ካሜሩን)
ሮቤርቶ ካርሎስ ሎፔዝ (ኬፕ ቨርድ)
ሚሼል ንጋድዉ ናጋጂዊ (ካሜሩን)
አማካዮች
አማኑኤል ዮሐንስ (ኢትዮጵያ)
አንድሬ ፍራንክ ዛምቦ አንጉይሳ (ካሜሩን)
ኢስሜይላ ኦውድራጎ (ቡርኪና ፋሶ)
አጥቂዎች
ቪንሰንት አቡበከር (ካሜሩን)
ሀሳኔ ባንዴ (ቡርኩና ፋሶ)
ካርል ብሪልያንት ቶኮ (ካሜሩን)
– የምድብ ሀ ኮከብ ተጫዋች ቪንሰንት አቡበከር (ካሜሩን) ሆኗል።
– አማኑኤል ምንም እንኳን የምድብ ሀ ምርጥ አስራ አንድ ውስጥ ቢካተትም የአጠቃላዩ የምድብ ጨዋታዎች ምርጥ አስራ አንድ ምርጫ ውስጥ ሳይካተት ቀርቷል።