​ከታንዛኒያ አቻው ጋር ጨዋታ የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰላለፍ ወጥቷል

የዓለም ዋንጫ የአራተኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታውን ከደቂቃዎች በኋላ የሚያደርገው የኢትዮጵያ ሴቶች ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ አሰላለፍ ይፋ ሆኗል።

በአሠልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል የሚመራው የኢትዮጵያ ሴቶች ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በኮስታሪካ አስተናጋጅነት ለሚከናወነው የዓለም ዋንጫ ለማለፍ ሁለት የ180 ደቂቃዎች ፍልሚያ ብቻ እንደቀሩት ይታወቃል። የአራተኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታውን ከሜዳው ውጪ ለማድረግ ከትናንት በስትያ ወደ ዛንዚባር ያቀናው ቡድኑ አስር ሰዓት ሲል የታንዛኒያ አቻውን ለመግጠም የመረጠውን የመጀመሪያ አሰላለፍ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል።

ግብ ጠባቂ      

እየሩሳሌም ሎራቶ  

ተከላካዮች

ብዙዓየሁ ታደሠ       

ብርቄ አማረ 

ቤቴልሔም በቀለ 

ናርዶስ ጌትነት                              

አማካዮች 

ኚቦኝ የን  

ገነት ኃይሉ            

መሳይ ተመስገን   

አጥቂዎች     

አርያት ኦዶንግ  

ቱሪስት ለማ                       

ረድኤት አስረሳኸኝ 

ያጋሩ