ከታህሳስ አጋማሽ ጀምሮ በባቱ ከተማ ሲደረግ የነበረው የ2014 የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ ውድድር የመጀመሪያው ዙር ቀሪ መርሐ-ግብር በሀዋሳ ከተማ ይቀጥላል።
መጠሪያ ስያሜውን በመለወጥ ከታህሳስ 16 እስከ ጥር 12 ድረስ በባቱ (ዝዋይ) ከተማ ሲደረግ የሰነበተው የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ የ2014 የውድድር ዘመን የመጀመሪያው ዙር ሰባት ሳምንታት ጨዋታዎችን በባቱ ስታዲየም እና በሼር ኢትዮጵያ ሜዳ ሲደረግ ከርሞ ነበር። ባሳለፍነው ሳምንትም የመጀመሪያው ዙር የሰባት ሳምንታት 49 መርሐ-ግብሮችን አከናውኖ ያገባደደ ሲሆን የዚህን ዙር ቀሪ ስድስት ጨዋታዎች ደግሞ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአራት ከተሞች ላይ ውድድሩን ለማድረግ ባቀደው ዕቅድ መሠረት በሀዋሳ ከተማ የመጀመሪያው ዙር የመጨረሻ ጨዋታዎችን ለማድረግ የወሰነ መሆኑ ታውቋል። ከጥር 28 ጀምሮም ውድድሩ በሀዋሳ አርቴፊሻል እና ግብርና ሜዳዎች ላይ እየተደረገ እስከ የካቲት 23 ድረስ የሚዘልቅ ይሆናል፡፡
በባቱ በነበሩ ውድድሮች ከልምምድ እና ከውድድር ሜዳ ጋር በተገናኘ ቅሬታ ሲነሳበት የነበረው የሴቶች የከፍተኛ ሊግ ውድድር የአንደኛው ዙር ከተጠናቀቀ በኋላ የሴቶች ልማት እና ውድድር ኮሚቴ የሁለተኛውን ዙር መርሐ-ግብርን በባህርዳር ፣ አዳማ አልያም በድሬዳዋ ከተማ ለማድረግ ዕቅድ እንደያዘ ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች፡፡
በባቱ በተደረጉ የሰባት ሳምንታት ጨዋታዎች ላይ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በመሪነት ያጠናቀቀ ሲሆን ቀሪ የስድስት ሳምንት ጨዋታዎችን በተከታይ መልኩ አቅርበንላችኋል፡፡
8ኛ ሳምንት
ጥር 28
አሰላ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ወጣቶች አካዳሚ (3፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)
ሀላባ ከተማ ከ ልደታ ክፍተከተማ (4፡00 ግብርና ሜዳ)
ቂርቆስ ክፍተከተማ ከ ሲዳማ ቡና (5፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)
ሰበታ ከተማ ከ አራዳ ክፍለከተማ (10፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)
ጥር 29
ንፋስ ስልክ ላፍቶ ከ ለሚ ኩራ (3፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)
ሀምበሪቾ ከተማ ከ ሱሉልታ ከተማ (5፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)
ለገጣፎ ከተማ ከ ፋሲል ከነማ (10፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)
9ኛ ሳምንት
የካቲት 03
ኢትዮጵያ ወጣቶች አካዳሚ ከ ለገጣፎ ከተማ (3፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)
ፋሲል ከነማ ከ ሀምበሪቾ ከተማ (4፡00 ግብርና ኮሌጅ)
ለሚ ኩራ ከ ሀላባ ከተማ (5፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)
ሲዳማ ቡና ከ አሰላ ከተማ (10፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)
የካቲት 04
አራዳ ክፍለከተማ ከ ቂርቆስ ክፍለከተማ (3፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)
ልደታ ክፍለከተማ ከ ሰበታ ከተማ (5፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)
ሱሉልታ ከተማ ከ ንፋስ ስልክ (10፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)
10ኛ ሳምንት
የካቲት 08
ሀላባ ከተማ ከ ሱሉልታ ከተማ (3፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)
አሰላ ከተማ ከ አራዳ ክፍለከተማ (4፡00 ግብርና ሜዳ)
ንፋስ ስልክ ከ ፋሲል ከነማ (5፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)
ቂርቆስ ክፍለከተማ ከ ልደታ ክፍለከተማ (10፡ አርቴፊሻል ሜዳ)
የካቲት 09
ለገጣፎ ከተማ ከ ሀምበሪቾ ከተማ (3፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)
ኢትዮጵያ ወጣቶች አካዳሚ ከ ሲዳማ ቡና (5፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)
ሰበታ ከተማ ከ ለሚ ኩራ (10፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)
11ኛ ሳምንት
የካቲት 13
ልደታ ክፍለከተማ ከ አሰላ ከተማ (3፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)
ሲዳማ ቡና ከ ለገጣፎ ከተማ (4፡00 ግብርና ሜዳ)
ለሚ ኩራ ከ ቂርቆስ ክፍለከተማ (5፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)
ፋሲል ከነማ ከ ሀላባ ከተማ (10፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)
የካቲት 14
ሀምበሪቾ ከተማ ከ ንፋስ ስልክ ላፍቶ (3፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)
ሱሉልታ ከተማ ከ ሰበታ ከተማ (5፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)
አራዳ ክፍለከተማ ከ ኢትዮጵያ ወጣቶች አካዳሚ (10፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)
12ኛ ሳምንት
የካቲት 17
ሲዳማ ቡና ከ አራዳ ክፍለከተማ (3፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)
ቂርቆስ ክፍለከተማ ከ ሱሉልታ ከተማ (4፡00 ግብርና ሜዳ)
ኢትዮጵያ ወጣቶች አካዳሚ ከ ልደታ ክፍለከተማ (5፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)
አሰላ ከተማ ከ ለሚ ኩራ (10፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)
የካቲት 18
ሰበታ ከተማ ከ ፋሲል ከነማ (3፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)
ለገጣፎ ከተማ ከ ንፋስ ስልክ ላፍቶ (5፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)
ሀላባ ከተማ ከሀምበሪቾ ከተማ (10፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)
13ኛ ሳምንት
የካቲት 22
ልደታ ክፍለከተማ ከ ሲዳማ ቡና (3፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)
ለሚ ኩራ ከ ኢትዮጵያ ወጣቶች አካዳሚ (4፡00 ግብርና ሜዳ)
ሱሉልታ ከተማ ከ አሰላ ከተማ (5፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)
ንፋስ ስልክ ላፍቶ ከ ሀላባ ከተማ (10፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)
የካቲት 23
ሀምበሪቾ ከተማ ከ ሰበታ ከተማ (3፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)
አራዳ ክፍለከተማ ከ ለገጣፎ ከተማ (5፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)
ፋሲል ከነማ ከ ቂርቆስ ክፍለከተማ (10፡00 አርቴፊሻል ሜዳ)