የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የተወሰኑ ጨዋታዎች የሰዓት ለውጥ ተደረገባቸው

በነገው ዕለት የሚጀመረው የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች መጠነኛ የሰዓት ሽግሽግ ተደርጎባቸዋል።

የሀገራችን ትልቁ የሊግ እርከን የሆነው እና በቤትኪንግ ስያሜ እየተከናወነ የሚገኘው ውድድር ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ በኋላ በነገው ዕለት እንደሚጀመር ይታወቃል። የውድድሩ የበላይ አካል የሆነው አክሲዮን ማኅበር እና የቀጥታ ስርጭት ባለመብት ዲ ኤስ ቲቪ በድሬዳዋ ከተማ ካለው ሙቀት መነሻነት 10 እና 1 ሰዓት እንዲጀመር ንግግሮችን ሲያደርጉ የከረሙ ሲሆን ውይይቱም እስከ ዛሬ ከሰዓት ድረስ ዘልቆ አዲስ ውሳኔ መወሰኑን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

በዚህም ከዚህ ቀደም በድሬዳዋ የሚደረጉት ሁሉም ጨዋታዎች 10 እና 1 ሰዓት ላይ ይጀመራሉ የሚለው የቅዳሜ እና የእሁድ ጨዋታዎችን እንደማያካትት ታውቋል። ከአዘቦት ቀን ውጪ ያሉት ጨዋታዎችም 9 እና 12 ሰዓት እንደሚደረጉ አውቀናል። ለዚህ ምክንያት የተቀመጠው ደግሞ በሁለቱ የሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት የአውሮፓ ሊግ ጨዋታዎች ስላሉ እንደሆነ ተመላክቷል።